Cart

No products in the cart.

  • Home
  • Autobiography
Hot

መመለስ ቦጌ ትውስታዎቼ Memeles by Birtukan Mideksa

$25.00

Memeles A book by Birtukan Midekssa. Boge Tewestawoche – መመለስ ቦጌ ትውስታዎቼ

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በአቋም ጽናትና በአመራር ብቃቷ በምትታወቀው ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የተዘጋጀው “መመለስ፦ ቦጌ ትውስታዎቼ” የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል። ብርቱካን ሚደቅሳ በዚህ መጽሐፏ ታሪኳን የተረከችበት፣ ልምዷን ያካፈለችበት፣አስገራሚውን የሕይወት ታሪኳን አጋርታናለች።

Memeles book by Birtukan Midekssa

Birtukan Midekssa Publishing 9999009514 January 28, 2026 Amharic 306 pages

Authors

Meet the Author

Birtukan Mideksa

Book By Birtukan Mideksa View All
Memeles book by Birtukan Midekssa
መመለስ ቦጌ ትውስታዎቼ Memeles birtukan mideksa book

Description

… የመጻፍ ሂደቴ ደጋግሞ እየወሰደኝ ያለው … እገሌ ወደተባልኩባቸው፣ ወደ አደባባይ ማንነቶቼ አልሆነም። ገና አንቱ ሳልባል፣ ከገባኝ በላይ በሆነ የመወደድ ብርሃን ዐቅፎ አኑሮኝ፣ ለፍትሕ እንድፀንስ፣ ለሀገር መውደድ እንድፈግግ ወዳደረገኝ ወደዛ የመውጫ ቤቴ (መንደሬ ወይም ሰፈሬ ስለው ያንስብኛል) እንደገና፣ እንደገና ይመልሰኝ ጀመር። ጨረስኩ ስል ሌላ ታሪክ… አበቃ ስል ሌላ ንሸጣ …

ነገር ግን ይህን መጽሐፍ አስቀድሜ በማምጣት የአደባባይ ታሪኬ ለኅትመት እስኪበቃ (እሱ የሚቀር ነገር አይደለም) በዚህ አዝግሙ ማለቴም አይደለም፤ በፍጹም። ይልቁንም የአደባባይ ሆነ የግል፣ የወጣትነት ሆነ የጎልማሳነት እውነቶቼ ሁሉ አውራ የሆነው ዋና እውነቴ ይሄኛው መሆኑን በትሕትና ማሳየቴ እንጂ።

… ሳጠቃልለው በአጭሩ ግለጪያት ብትሉኝ መመለስ ብዙ ፍቅር እና ብርሃን ለሰጠኝ ማኅበረሰብ (ቤቴ) ለበጎነቷ የጽሑፍ ሐውልት አቁሞ ብድሯን ስለመመለስ ነች – መልሼ የምጨርሰው ባይሆንም። ደግሞም ጫጩቷ መታቀፍን እና ሙቀትን ፈልጋ ወደ እናቷ ጉያ እንደምትሮጠው ዓይነት፣ ከመከራ ጋ ተሞካክረን ባበቃንበት ጊዜያት ሁሉ ወደ ቤቴ ስለ መመለስ፣ ስለ መመላለስም ነች። በመጠኑ ደሞ ከጸለምተኛ ዘመኖቼ በጥረት ወደ ቀድሞ ጥንካሬ ስለመመለስ (resilience)። እያዋዛች ለእናንተ ሌላ፣ ሌላም ትርጉም የመስጠት ዐቅም ያላትም ትመስለኛለች። …

 

የብርቱካን ሚደቅሳ “መመለስ” መጽሐፍ

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በአቋም ጽናትና በአመራር ብቃቷ በምትታወቀው ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የተዘጋጀው “መመለስ፦ ቦጌ ትውስታዎቼ” የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል.

ብርቱካን ሚደቅሳ በዚህ መጽሐፏ ታሪኳን የተረከችበት፣ ልምዷን ያካፈለችበት፣አስገራሚውን የሕይወት ታሪኳን አጋርታናለች

Reviews

There are no reviews yet.

Be the first to review “መመለስ ቦጌ ትውስታዎቼ Memeles by Birtukan Mideksa”