- This event has passed.
የታሪክና የጥበብ ውህደት፡ “አክሊሉ” የታሪካዊ ልብ-ወለድ መጽሐፍ ምርቃት!
ታሪክን ከፈጠራ ጥበብ ጋር አዋህዳ በልዩ ሁኔታ የከተበችው ደራሲ ዶ/ር ሰላማዊት ታደሰ፣ “አክሊሉ” የተሰኘውን አዲስ ታሪካዊ ልብ-ወለድ መጽሐፏን ለንባብ ልታበቃ ነው።
ይህ በጸሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተ-ወልድ የሕይወት ታሪክ ላይ ተመርኩዞ የተጻፈው ድንቅ ልብ-ወለድ፣ የኢትዮጵያን የታሪክ ክስተቶች በልዩ የጥበብ ቀለም ስሎ ያቀርብላችኋል!
በዕለቱ የሚገኙ የክብር እንግዶች፡
ቴዎድሮስ አጥላው፦ ደራሲና ሐያሲ
ዋሊሁን በላይ፦ አርቲስት
የምረቃው መርሐ-ግብር፦
ቀን፦ ነገ ቅዳሜ መጋቢት 05 ቀን 2018 ዓ.ም.
ሰዓት፦ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ
ቦታ፦ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት (ወመዘክር)
የታሪክን እውነት ከልብ-ወለድ ጣዕም ጋር አጣጥሞ ለመቋደስ ነገ በወመዘክር እንገናኝ!
AddisBooks Ads