- This event has passed.
የዋልያ የሐሳብና መጽሐፍ መድረክ፦ የዓለም መቀዝቀዝ ለኢትዮጵያ ተስፋ?
ዎልያ መጻሕፍት ከፍተኛ የምሁራን ተሳትፎ የሚታይበትን ልዩ የውይይት መድረክ አዘጋጅቶላችኋል።
በዕለቱ “የዓለም መቀዝቀዝ ለኢትዮጵያ ተስፋ? የማምረቻ ኢንዱስትሪው እውነታ፣ ዕድሎችና አቅጣጫ…” በሚል ርዕስ በዘርፉ ሰፊ እውቀት ያላቸው ምሁራን ጥልቅ ትንታኔ ያቀርባሉ።
🎤 አቅራቢዎች፦
- ዶክተር አማረ ማተቡ (Dr. Amare Matebu)
- ዶክተር ብርሀኑ በሻህ (Dr. Berhanu Beshah)
🎤 አወያይ፦
- ጋዜጠኛ አብርሃም ታደሰ
የኢንዱስትሪውን የወደፊት ጉዞ፣ ዓለም አቀፋዊ ተፅዕኖዎችን እና የኢትዮጵያን ዕድሎች ለመረዳት ይህንን መድረክ እንዳያመልጥዎ!
የዝግጅቱ ዝርዝር፦
- ቀን፦ ቅዳሜ መጋቢት 5 ቀን 2018 ዓ.ም (ነገ!)
- ሰዓት፦ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ
- ቦታ፦ 4 ኪሎ፣ ኤክላስ ህንፃ፣ ዎልያ መጻሕፍት አዳራሽ
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል። በዕለቱ ተገኝታችሁ የሐሳብ ግብይት እንድታደርጉ በአክብሮት እንጠብቃለን።
AddisBooks Ads