ኑ! የታላቁን ድንቅ ስራ ልደት አብረን እናክብር!
የኢትዮጵያ ስነ-ጽሁፍ ቁንጮ የሆነው “ፍቅር እስከ መቃብር” የታተመበትን 60ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ፣ ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ ልዩና ደማቅ ፕሮግራምአዘጋጅቶላችኋል።
ይህ በክላሲክ ስራው ውስጥ ያሉትን እነ በዛብህና ሰብለወንጌልን፣ የዲማ ጊዮርጊስን ድባብና የሀዲስ ዓለማየሁን ጥልቅ ጥበብ የምንዘክርበት ልዩ መድረክ ነው።
የእለቱ ድምቀት – አቅራቢዎቻችን
የስነ-ጽሁፍና የታሪክ ሊቃውንት በአንድ መድረክ ተሰባስበው ይጠብቁዎታል፡
ሽብሩ ተድላ (ኤመረተስ ፕሮፌሰር)
ታዬ አሰፋ (PhD.)
ጌታቸው በለጠ
ሕይወት እምሻው
መአዛ ወርቁ
እሸቱ ጥሩነህ
እንዳለጌታ ከበደ
መቼ እና የት?
ቀን፦ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም (ቅዳሜ)
ሰዓት፦ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ
ቦታ፦ ቀበና፣ ካቶሊክ፣ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን አቅራቢያ (ወደ ሳንፎርድ ትምህርት ቤት በሚወስደው መንገድ፣ ባማ አዲስ ሕንፃ አጠገብ፣ FSS አዳራሽ)
ልዩ የሚያደርገው
ይህ ዝግጅት በክብር እንግዳው ዶክተር ያሬድ ኢሳያስ ከተጻፉት ሁለት መጻሕፍት ሽያጭ በተገኘ ገቢ የተደገፈ ሲሆን፣ ለስነ-ጽሁፍ አፍቃሪያን በሙሉ ጥሪው በነጻ ነው!
ታዲያ ምን ይጠበቃል? የጥበብ ጓደኛዎን ይዘው ይከሰቱ! ነገረ መጻሕፍት!
AddisBooks Ads