Loading Events
የዋልያ የሐሳብና መጽሐፍ መድረክ
ሀገር በቀል የሥነ-ፈለክ ምርምር
(Indigenous astronomy) እና ሥነ-ፈለክ እና አስትሮ-ፎቶግራፊ (Astronomy and Astro-photography) 
ከሰማይ ከዋክብት ጀርባ ያሉትን ረቂቅ ምስጢራት በሀገር በቀል ዕውቀትና በዘመናዊው የፎቶግራፍ ጥበብ ለመቃኘት ዝግጁ ኖት?
ዋልያ የሐሳብና የመጻሕፍት መድረክ፣ ልዩና አስደሳች በሆነው “ሀገር በቀል የሥነ-ፈለክ ምርምር” ርዕሰ-ጉዳይ ዙሪያ የዘርፉን ጥልቅ ዕውቀት ካላቸው ምሁራን ጋር ሊያገናኛችሁ ቀጠሮ ይዟል።
ምን ይጠብቅዎታል?

ጥንታዊው የሀገር በቀል አስትሮኖሚ (Indigenous Astronomy) ትርጉምና ፋይዳ።

የሰማይ አካላትን በምስል የማስቀረት አስደናቂው የአስትሮ-ፎቶግራፊ ጥበብ።

ከምሁራን ጋር የሚደረግ ጥልቅ የሐሳብ ልውውጥ።

የዕለቱ እንግዶቻችን፦

ዶ/ር ጌትነት ፈለቀ (ከባሕል አስትሮኖሚ ዕውቀት አንጻር)

አቶ ክብረት አፅበሃ (አስትሮኖሚ እና አስትሮ-ፎቶግራፊ)

🎤 አወያይ፦ ምግባር ሲራጅ

🗓️ መቼ፦ ቅዳሜ መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም
ሰዓት፦ ከሰዓት 8፡00 ጀምሮ
📍 ቦታ፦ 4 ኪሎ፣ ኢክላስ ሕንፃ፣ ዋልያ መጻሕፍት አዳራሽ

“ኑ እንወያይ፣ ሐሳብን ለሐሳብ እናካፍል!”

ባሕላዊ ዕውቀታችንን ከዘመናዊ ሳይንስ ጋር አቀናጅተን የምናይበት ይህ ልዩ መድረክ እንዳያመልጥዎ። ቅዳሜዎን በዕውቀትና በግርምት ያሳልፉ!

Location

Location
Walia bookstore ዋልያ መጻሕፍት
Address
Arat Kilo
Addis Ababa, Ethiopia

Leave a Reply

AddisBooks Ads