Description
ኤክሶድያ Exodia by Solomon Abebe
ደራሲ ሰሎሞን አበበ በኤክሶድያ መጽሐፍ በቦታው ተገኝቶ ከጅማ በመነሳት ከመካከለኛው ምስራቅ እስከ ካናዳ ያጠናውን እውነተኛ የስደት ታሪክ በተዋበ ልቦለዳዊ ስነ ፅሁፍ አስፍሯል፡፡ አንባቢ በምናቡ ያልኖረበትን የስደት ጣእም እንዲያጣጥም መከራውን እንዲቀምስ ያስቻለበት ድንቅ መጽሐፍ ነው።
የታሪኩ ዋነኛ ገጸባህርያት ፍቅር፤ ስደት፤ እስራት፤ ስራና ኑሮን ተከትሎ ለኢትዮጵያውያን የስደት ምክንያት የሆነውን በአገር ውስጥ ሰርቶ ለመኖር ያለውን ውጣ ውረድ፤ የምስራቁን የሕገ ወጥ ስደት መስመር በመከተል በሶማሊ ላንድ፤ የመን፤ ሳዑዲ፤ ሊባኖስ፤ ባህሬን፤ ኩዌት፤ ጅቡቲ፤ ኬንያ እና ካናዳ ያሻግረናል፡፡ ለድህነት ምክንያቶችን ከገጠር እስከ ከተማ ያለውን መዋቅር በመሄስ መፍትሄውንም በማመላከት የተሸለ ነገን ያሳየናል፡፡ቀልብን በሚስብ ስነ ጽሁፍ በእውነተኛ ስደተኞቹ ጫማ ውስጥ ሁነን የኑሯቸውን ከፍታና ዝቅታ አብረን እየተቋደስን የህይወትን ትርጉም እንድናመሰጥር ያደርጋል፡፡
ወሰን ባዩ (ዶ/ር)
ጋዜጠኛ እና የስነ ጽሁፍ መምህር
Reviews (0)
You must be logged in to post a review.
Liyu Ken New Zare - Ethiopian Music
AddisBooks Ads
AddisBooks Ads

Reviews
There are no reviews yet.