- This event has passed.
ታላቅ የመጽሐፍ ፊርማ ሥነ-ስርዓት!
የንባብ ባህል እንዲዳብርና የጥበብ መንደር እንድትጎለምስ ዘወትር የሚተጋው ጃዕፈር መጻሕፍት፣ አዲስና በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን የደራሲ አዛርያስ ደሴ ልብ አንጠልጣይ ልቦለድ “ካራሞን” አስመልክቶ ልዩ የፊርማና የፎቶ ፕሮግራም አዘጋጅቶላችኋል።
በአዳኝና ታዳኝ ግብግብ በተሞላው ዓለም ውስጥ ፍቅርን፣ እጣፈንታን፣ ምስጢርንና ያልተነገሩ ኢትዮጵያዊ ታሪኮችን በግርማ ሞገስ የያዘውን ይህንን ድንቅ ስራ ከራሱ ከደራሲው እጅ አስፈርማችሁ ለመውሰድና የማይረሳ የፎቶ ትውስታ ለማስቀረት ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
📆 ቀን፦ ቅዳሜ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም
⏰ ሰዓት፦ ከቀኑ 8:00 እስከ 10:00 ሰዓት
📍 ቦታ፦ አዲሱ ጃዕፈር መጻሕፍት – ለገሃር፣ ተወልደ ሕንጻ ስር
⏰ ሰዓት፦ ከቀኑ 8:00 እስከ 10:00 ሰዓት
📍 ቦታ፦ አዲሱ ጃዕፈር መጻሕፍት – ለገሃር፣ ተወልደ ሕንጻ ስር
«የንባብ ባህል እንዲዳብር እንተጋለን!»
📞 ለበለጠ መረጃ፦ 0911 125324