Cart

Authors

  • Home

Author Dagmawi Amelewerk

ይህ ሰው ትንሽ ትልቅ ሳይል  ሁሉን አክባሪ እና ልበ ቀና ትሁት ሰው ነው፡፡ ነገርን ማቅለል እና የተወሳሰበ ነገር የማይወድ የቴአትር ባለሙያ፡፡ዳግማዊ ዓመለ ወርቅ ፈይሳ በ1960 ዓ.ም አ.አ አብነት አካባቢ ጠጅ

Author's Books

Deciding What to Read Next?

Description

ይህ ሰው ትንሽ ትልቅ ሳይል  ሁሉን አክባሪ እና ልበ ቀና ትሁት ሰው ነው፡፡ ነገርን ማቅለል እና የተወሳሰበ ነገር የማይወድ የቴአትር ባለሙያ፡፡ዳግማዊ ዓመለ ወርቅ ፈይሳ በ1960 ዓ.ም አ.አ አብነት አካባቢ ጠጅ ሳር ሰፈር ተወለደ፡፡ ቄስ ትምህርት ቤት ተምሯል፡፡የመጀመሪያ ደረጃ ከ 1-8ኛ ክፍል በወሰን ሰገድ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምሀርቱን  መድኀኒአለም አጠቃላይ 2ተኛ ደረጃ ትምሀርት ቤት ተከታትሏል፡፡ከ1-5ኛ ክፍል ቁጥር ላይ ጎበዝ የሆነ የሂሳብ ተማሪ ነበር፡፡ 5ኛ ክፍል ቤሳ ልቦለዶችን ማንበብ ጀመረ ። ከአድማስ ባሻገር የመጀመሪያ ትዝታው ነው፡፡ የ7ተኛ ክፍል ተማሪ ሆኖ ግጥሞችን መጻፍ ጀመረ፡፡ 9ኛ ክፍል ‹‹ደማቅ ህይወት›› ልቦለድ መፅሐፉን ፃፈ፡፡ ሲኒማ ኢትጵያ፤ ሲኒማ ኢምፓየር መገኛ ቦታዎቹ ሆኑ፡፡

የኢትዮጵያ ሬዲዮ ፕሮግራሞች አያመልጡትም፤ ሙዚቃ በጣም ያዳምጣል፡፡  እግር ኳስ መጫወት ይወድ ነበር ፤  እሱ ያለበት የሰፈር ቡድን የአካባቢውን ዋንጫ እስከመውሰድም ደርሷል፡፡አባቱ መፅኀፍ ገዝተው ያመጡለታል፤  ጮክ ብሎ ሲያነብላቸው 10 ሳንቲም ወይም 25 ሳንቲም በመሸለም ያበረታቱት ነበር፡፡ አልወለድም ለመጀመሪያ ጊዜ  የተበረከተለት መፅሐፍ ነው፡፡

አ.አ ዩ ሲገባ ምርጫው ቴአትር ሆነ ፡፡ የ2ተኛ ዓመት ተማሪ ሆኖ ለመጀመሪያ ጊዜ መድረክ ላይ ወጣ። በሂደትም በርካታ ስራዎችን ሠርቶ ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ አ.አ ማዘጋጃ ቤትን ተቀላቅሎ ያላቻ ጋብቻ፣ ነቃሽን፣ ማደጎንና የሊስትሮ ኦፔራን ቴአትሮችን ሰርቷል፡፡ከ1983 በኋላ በወቅቱ የነበረው የፖለቲካ ስርዓት ስላልተመቻቸው አባተ መኩሪያ ፤ ፍቃዱ ተ/ማርያም እና ዳግማዊ ዓመለወርቅ ፈይሳ  ከማዘጋጃ ቤት  ስራቸውን   ለቀው ወጡ፡፡ ኤዲፐስ ንጉስን ብሄራዊ ቲያትር ቤት ለእይታ አበቁት፡፡


ብዙዎች በአድናቆት ያጨበጨቡለት እና ለ2ተኛ ጊዜ ብሄራዊ ቴአትር የታየው የኮከቡ ሰው ቴአትርን አዘጋጀ። በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ታይቷል፡፡  ጋሽ ተስፋዬ ገሰሰ፣ ዳግማዊን ባህል ማዕከልን እንዲቀላቀል ጥሪ አቀረበለት፤ እሱም የማዕከሉ art section chief ( የኪነጥበብ ኃላፊ) ሆኖ በ4 ዓመት ቆይታው  ከአስራ ሁለት በላይ የሙሉ ጊዜ ቲያትሮችን አዘጋጅቷል፡፡
ትልቁ የህይወቱ ክፍል በሜጋና ሀሌታ ማስታወቂያ ድርጅቶች ውስጥ ጀመረ፡፡

ለ17 ዓመታት ያህል ስክሪፕት በመጻፍ፤ ከ 500 በላይ ዶክመንተሪዎችንና 1000 ማስታወቂያዎችን  ሠርቱዋል፡፡ ግጥሞችን ፤ ልቦለዶችን ይጽፋል፡፡ 2005 ላይ ማስትርሱን በአ.አ.ዩ  በtheatre and development አጠናቀቀ ፤ ለ5 ዓመት በመምህርነት አገለገለ፡፡ ዓመል የቴሌቭዥን ድራማ፤ የቃቄ  ውርዶዎት ትውፊታዊ ቴአትርን አዘጋጅቷል፤ ብሔራዊ ቲያትር ለ3 ዓመት ተኩል ያህል ታይቷል፡፡ የቃቄ ውርዶት፤ ከመጋረጃ ጀርባ፤ አልቢኖ፤ እና የኮከቡን ሰው በተለየ እንደሚወዳቸው ይናገራል፡፡ ‹‹የቴአትር ዝግጅት ለእኔ እንደገና ህይወትን መፍጠር ነው›› ይላል ዳግማዊ።

በስራው በርካታ ሽልማቶችን አግኝቷል፡፡በ2004 ዓ.ም ምርጥ የቴአትር  አዘጋጅ  በአንደኝነት ዋንጫ ተሸላሚ በ2005
ዓ.ም ለአ.አ 125ኛ ዓመት ክብረ በዓል የቴአትሮች ውድድር ምርጥ የቴአትር  አዘጋጅ  በአንደኝነት ዋንጫ ተሸላሚ፣ 2013 ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ባዘጋጀው የስነ ጥበባት ውድድር በቴአትር አዘጋጅነት  በአንደኝነት የወርቅ ሜዳሊያ፤ የዋንጫ፤ የዲፕሎማ እና የመቶ ሺ ብር ተሸላሚ፡፡

ከ40 በላይ በሚሆኑ የመድረክ ቴአትሮች ውስጥ በትወና በዝግጅትና በድርሰት ተሳትፏል፣

የኪውፒድ ቀስት፡- የዶጋሊ ቁጭት፣አማጭ፡- መንበረ ደይን፡ዶን ጁዋን፡- እድምተኞቹ፡- እንግዳ፡- ጥላ፡- ቴአትር ሲዳዳ፡- ማደጎ፡- የማታለቅሰው ሕፃን፡- ሎሩሀማ፡- የዓምላክ ባለሟል፡- ደባ፡- ያላቻ ጋብቻ፡- ነቃሽ፡- ኤዲፕስ ንጉሥ፡- የኮከቡ ሰው፡- የሻማ እንባ፡- ከአድማስ ባሻገር፡- በላይ ዘለቀ፡- ኦማር ካያም፡- መስተፋቅር፡- ቤተሰቡ፡- ፡፡የቃቄ ውርድወት፡- ዋዜማ ሐምሌት “ከመጋረጃ ጀርባ”፣ የሊስትሮ ኦፔራ፡- አልቢኖ፡- የባላገር ፍቅር፡- አዳብና፡-

ቲቪ ድራማና ፊልሞች
አጋጣሚ- የዘማሪዋ ወፍ ህልም፡- ጥምጥም፡- ሦስተኛው መንገድ፡-የዳቦ ገረድ፣ መቅረዝ; አመል  ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ

ሬዲዮ ድራማ
ጥያቄ፣  ሽሽት፣  የደወል ድምፆች፡- እሽክርክሪትፅልመትና ውበት፡- ክፍተት፣ ዘሀ፣ ራዕይ ባላንጣ፡- የአዛውንቶች ክበብ ቁጥር 2፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ልጅ

Review

Customer Reviews

Write A Review

AddisBooks Ads