ከአመጿ ጀርባ Ke Ametsua Jerba by Eden Habtamu
$25.00
ከአመጿ ጀርባ Ke Ametsua Jerba, a book by Eden Habtamu.
Addis Books!
Description
ከአመጿ ጀርባ Ke Ametsua Jerba by Eden Habtamu
Ke Ametsua Jerba (ከአመጿ ጀርባ) is a contemporary Amharic fiction novel by author and journalist Eden Habtamu.
ከመፅሐፉ በጥቂቱ….
“….. በ1960ዎቹ ላይ ያለ ዘናጭ ዘመናዊ ጎልማሳ፣ የጊዜ ሂደትን በአንዳች ምትሀት ማቆም ቢችል፤ እንደ’ሊቁ’ መኖር የሚችል ይመስለኛል። ቤቱ ግድግዳው ላይለጌጥነት የለጠፈው የአዲስ ዘመን እና የዛሬዪቱ ኢትዮጲያ ጋዜጣ፣ እዚያ ዘመን ላይ ያለ ሰው አስመስሎታል። በዕድሜ የእኔ እኩያ የሚመስል ሰፋ፣ በእጅ የተላገ ወዝ የጠገበ የማእድ ጠረጴዛው፣ አራት ዘመናቸውን በድሎት ያሳለፉ የመሬት ሳንቃ ላይ ቦታ ቦታቸውን ይዘው ተቀምጠዋል። ቤቱ ከውጪ ሲታይትንሽ ቢመስልም፣ ውስጡ ከበቂ በላይ ነበር። ሦስት ወዛም ቅጠል ያላቸው የቤት ውስጥ አትክልቶች፣ ጥግ ጥግ ይዘው ተቀምጠዋል።
ወደ ግራና ቀኝ የሚከፈቱት መስኮቶች በተከፈቱና በተዘጉ ቁጥር የሚያሰሙት የራሳቸው የአኮርዲዮን ድምጽ አላቸው። የአገልግሎት ዘመናቸውንና፣ ልፋታቸውን፣ ያዩትን ጉድ፣ አፍ አውጥተው፣ ይናገራሉ። ጺ…….ጥ……….ጥ…ጥ.ጥጥ ግው ግድግዳው ላይ!
ወደ ሊቁ ስዞር፣ መኪና የረሱ የሚመስሉ ጠንካራና ረጃጅም እግሮች፣ እንደ ባህርዛፍ ቀጥ ያለ፣ ብዙ ያሳለፈ የሚመስል ከጠንካራ አጥንት እና ጅማት የተዋቀረ፣ ለሥጋ ብዙም ቦታ የሌለው ሰውነት ለብሶ ቀጥ ብሎ ቆሟል። እዚህ ሰውዬ አካባቢ እፍረትና ይሉኝታ የሉም። ለነገሩ አመጸኛ ምን እፍረትና ይሉኝታ አለው። እዚህ. ግን ይብሳል። እኔ ካልደከመኝ፣ እንደሙዚየም ቅርስ ሁሉ ላየው እችላለሁ። እሱም ሁኔታዬ ላይገርመው ይችላል። አዎን፤ ሰውየው አንድ መሰረታዊ ችግር አለበት፤ የመገረም እጥረት። በሚያናድድ መልኩ፣ ምንም አይገርመውም፤ አይደንቀውም። በረጃጅም ጣቶቹ እየቀነጣጠሰ የሚከትፈውን ጎመን ስመለከት ከጓዳ የራቅኩኝ ያህል ተሰማኝ። እሱን ለማገዝ ይቅርና፣ ይሄንን ትንሽ ሙዚየም የሚመስል ቤት እና ድባቡን ለማየትና ለመጨረስ ጊዜው አልነበረኝም። በዚህ የሚገርም የተለየ ዓለም ውስጥ፣ በቁጥር የታሰረ ጊዜ የለም። ጥድፊያና ወከባ የለም።ሁሉም ነገር መሬት ሰክኖ ተቀምጧል። መታዘዝ ሲኖርበት፤ የሚንቀሳቀስ ጀልባ ይመስላል።
ሦስቱ ግዙፍ ውሾች ምንጣፍ ላይ ጋደም ብለዋል። ከውሾቹ ራቅ ብሎ ሁለት ትልልቅ ዘመን ጠገብ ሳጥኖች፣ በሠረገላ ቁልፍ ተቆልፈው ተቀምጠዋል። ውስጣቸው አንዳች ቁም ነገር እንዳለ ግልጽ ነው። ጠጋ ብዬ እንደመሽኮርመም እያደረገኝ ዳበስኳቸው። በማባበል እና በማግባባት ዓይነት።አዎን ፣ሳጥኖቹ አሽኮረመምኳቸው።ምን ችግር አለው?ከፍቼ እንዳያቸው ከፈቀዱልኝ?!ምናልባትም በቤቱ ያሉ ብቸኛ የሚሽኮረመሙ ነገሮች እነሱ ይመስሉኛል።
Reviews (0)
You must be logged in to post a review.
AddisBooks Ads



Reviews
There are no reviews yet.