Description
ሸሙኔ (Shemune) by Mesfin Wondwossen
” Shemune is more than a novel — it is a celebration of Ethiopia’s rural heritage, a tribute to its linguistic diversity, and a window into its cultural philosophy. Mesfin Wondwossen has crafted a narrative that is at once deeply personal and universally resonant, blending humor, history, and heartfelt emotion. Whether you are a lover of literature, a student of sociology, or simply someone curious about Ethiopia’s cultural roots, Shemune is a must-read. It will leave you reflecting on the power of language, the importance of tradition, and the timeless nature of community.”
— Habtamu Alemu, Ethio Eyewitness

“ሸሙኔ በጥሩ የልቦለድ ቅርጽ የተገነባ፣ ለዛና ውበት በሞላው ጥልቅ የባላገር ዐማርኛ የተኳለ፣ በቆንጆ አተራረክ የተደራጀ የሚደነቅ ሥራ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፡፡ ደግሞም በጨዋታ የተሽሞነሞነ፡፡ ሸሙኔ መጽሐፍ ብቻ አይደለም፣ ሸሙኔ አገርም ነው፡፡ በፍቅር እስከ መቃብር የጎጃምን ባህልና ወግ እንዲሁም የያኔውን ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ሥርዓት እንደ ሲኒማ ቁልጭ አድርገን አየን፡፡ በጉንጉን እና አደፍርስ ደግሞ የሸዋን፡፡ በሌሎችም ድንቅ መጽሐፍት የሌሎችን፡፡ ሸሙኔ ዐማራ ሣይንት ይዞን ይገባል፡፡ ሸሙኔን ማንበብ ዐማራ ሣይንትን ቁጭ ብሎ በነጻ ማሰስ ነው። እዛ ውስጥ በምናብ ተቀርፆ የሚቀር አስደማሚ መልክአምድርና ስፍራ አለ፡፡ ባህል፣ ልማድ፣ ማኅበራዊ ሥነ-ልቦናና ሥርዓታዊ ሽግግር አለ፡፡ በከተሜው ዘንድ በስልጣኔ ስም በቃላት ደህይቶ የሚታየን ዐማርኛችን ተዝቆ የማያልቀው ውበቱ፣ ጥልቀቱና ሀብቱ ሸሙኔ በተመቸተበት ዐማራ ሳይንት ውስጥ እንደ ልብ ይፈሳል፡፡ ሸሙኔ ሊነበብ የሚገባው፣ ብዙ ሊባልለት የሚችል ሥራ ነወ፡፡ ከልብ የተደከመበት መሆኑ ያስታውቃል፡፡”
— አብርሃም ገነት (ደራሲ)
Reviews (0)
You must be logged in to post a review.




Reviews
There are no reviews yet.