Cart

  • Home
  • Poetry

የብርሃን ጥሞና by Saba Sisay 

$25.00

የብርሃን ጥሞና Ye Birhan Temona a book by Saba Sisay.
Addis Books!
978-99990-0-976-8 January 6, 2026 Amharic 112 pages

Authors

Meet the Author

ሳባ ሲሳይ Saba Sisay

Book By ሳባ ሲሳይ Saba Sisay View All
የብርሃን ጥሞና by Saba Sisay 
የብርሃን ጥሞና by Saba Sisay 

Description

የብርሃን ጥሞና by Saba Sisay 

የብርሃን ጥሞና በጥር ወር 2018 ዓ.ም ለአንባቢ የቀረበ ሲሆን በውስጡ ስድሳ /60/ ግጥሞችን አካቷል.ይህ መረጃ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በአንባቢ ዘንድ ጥሩ ተወዳጅነትን ያተረፈ ሲሆን በቀጣይም ገጣሚዋን ለበርካታ አንባቢ የሚያስተዋውቅ እንደሚሆን ከወዲሁ ተስፋ ሰጥቷል በመጽሐፍ መግቢያዋ ለመግለጽ እንደሞከረችው በግጥም ይዘት የተዳሰሱትን በርካታ ሀሳቦች እሷ ብትጀምራቸውም አንባቢ በራሱ ልክ ሀሳቡን ጨምሮ በአሻራው መልክ ፍጻሜ እንዲሰጣቸው ጋብዛለች

በ112 ገጽ ብዛት 60 ግጥሞችን ይዛ የመጣችው የሳባ ሲሳይ የግጥም መድብል ‘የብርሃን ጥሞና’ ቀልቤን ገዝታኛለችና ጥቂት ልበልላት። የግጥም የውበት ልዩነት ከሁሉ የስነ-ፅሁፍ አይነቶች ቀመር በተለየ በተሳበ ውል ዘርፉ እየተከታተለ አለመተርተሩ፤በዚ ቢያበቃ በዛ ቢጀመር ተብሎ አለመመተሩ ነው።የገጣሚዋ የድንቅ ቀን ጅማሮ ‘አቦል ቡና’ አልያም ነፍሷ ሀቅ ተጠምታ በተቸነከረችበት ለልመናዋ የተጋተችውን ‘የክፋት ሬት’ የምታስውብበት የቃል ሸማ ፈትል ነው።ስለዚህ ይህ ጥበብ የማንነቷ ክታብ ነው።
ልፍስፍስ ናት ብላ አለም እንዳትገፋኝ
አከሰርሽኝ ብሎ እግዜር እንዳይተፋኝ
ሰብረሽኝ ስትሄጂ መጠገንን አወቅኩ
ወደ እንባ ባህር በገፈተርሽኝ ልክ በሳቅ ጎዳና ፊት
ልመና ተሰለፍኩ
( ይህ ህይወቷ ባጭሩ ለተቀጨችባት ልጇ ንሴብሖ መታሰቢያ የተባለ ነው)
በግጥሞቿ መዝጊያ የተከተቡበት ቀን ሲሰፍር በብዙዎቹ ላይ ዓ/ዘ የሚል ቃል እናገኛለን ይህ የዘላለምነት ምህፃር የብርቱ መሆን የሁሉ ዞሮ መግጠም ምሳሌዋ ማርኮኛል….።በሀሳቦቿም በእይታዎቿም በቅኔ ጥበቧም ከእድሜ ቀን ቁጥር ስፍር ማለፍ፣ከሀዘን ስብራት ማገገም፣ደግሞ ለመሠበር በቀናነት መጋደምን፣በስብራቷ ፊትለፊት በውድቀት ዳጥ መሀል ተስፋን ለመቀንበብ ለፍቅር መታደምን፣ሁሉ ልክ እንዳሎነ በትህትና መሞገት እና በእምነት ደሞ መዝለቅን ልብን በሚሰቅዙ ሀዘንን በሚያወርሱ ወኔን በሚቀሰቅሱ ቃላት ከትባልናለች….!
” እንገናኛለን”
ይላል በሙሉነት ሞትን ሳይጠረጥር መቅረትን ሳያክል
ሁሉ መንገድ ወስዶ ይመልስ ይመስል
ግን እኔ አላመንኩም
አለመዞር ‘ንጂ ሌሊትና ቀንን
በምድር ዛቢያ ላይ ለደቂቃ ሚያትም
ከዞሩ በኃላ አለመፈራረቅ መቼም አይታለም።
ገፅ-61
በሀሳቦቿ መሀል ምትሞግታቸው ምትጠይቃቸው ለመሆናቸውም ላለመሆናቸውም ምታሳምንባቸው ጠንካራ እይታዎቿን ላሳያቹ በተረትና ዘመን ግጥሟ ዝም አልልም ዝምማ ይነቅዛል ለዛሬ ዘመኔ አዲስ ተረት ያሻል አይነት ሀሣብ ታነሳለች።ማራኪ ናት!በጨረፍታ እንዲ ትላለች…..
እንኳንስ ገልጠንው በጭፍን አይናችን ሰቆቃ እየገባ
እንዴት ዝም እንበል?
እንዴት ገሳ ለብሰን ሞትን እንከለል?

የትላንት ወጉን እንደአዋዜ ጠቅሰን ብንጎርሰው ለዛሬ
መች ሊሆን ወጌሻ ? መቼ ሊያሽርልን ኑሮ ስብራቱ
እያደር ያመናል ሀቅ ግርፋቱ
ገፅ-89
“በመግቢያዋ ግጥምና ስዕል በቃንን አያውቁም::”ትላለች በመድብሏም ስለሰአሊና ስዕል ብዙ ብላለች በዛም በጥበቡ አያይዛ የጥያቄ አይነት ታዘንባለች መጠየቋ በደፋር ሀሳብ አዲስ እይታን መናፈቋን የሚያሳዩ መስመሮች ጀባ ልበላቹ
ቆጨኝ ቁጭት ….
ቁጭት? ቁጭት ግን ምንድነው?
ቁጭት ነው አይደለ የትላንትና ህመም?
እያመረቀዘ እየሞላ መግል
በገለማ ቁጥር ዛሬን የሚያጋድል
ገፅ-96

Reviews

There are no reviews yet.

Be the first to review “የብርሃን ጥሞና by Saba Sisay ”
AddisBooks Ads