“ትናንታችን ውስጥ ያለፍነው ዛሬ አለ፤ ነጋችን ውስጥም ዛሬ ሕያው ሆኖ ይኖራል። በሕይወት ዑደት ሽቅብ ቁልቁል እንወጣለን፣ እንወርዳለን፣ እናጣለን፣ እንቀበላለን . . .ፀሐይ ትገባለች፣ ትወጣለች – ሰዓቷን ጠብቃ በዛቢያዋ ላይ እየተሽከረከረች! ትናንታችን ዝምታም ነው – አጠንክሮን፣ አስተምሮን የሚያልፍ፤ ዘወር ብለን ስናየው በዐይናችን የምንስመው . . . የምንዘክረው!” የሚሳም ተራራ
አንጋፋው ደራሲ ፍቅረማርቆስ ደስታ የሐመር ሕዝብ ባህል ላይ ባተኮሩት እጅግ ተወዳጅ በሆኑት ተከታታይ ‘ኤትኖግራፊክ’ ልብወለድ ድርሰቶቹ ይታወቃል። አሁን ደግሞ “የሚሳም ተራራ” የተሰኘ ድንቅ መጽሐፉን ለበርካታ ዓመታት በጉጉት ሲጠብቁ ለነበሩት አንባቢዎቹ ይዞ ቀርቧል። በዚህም የግለታሪክ መጽሐፉ ፍቅረማርቆስ የሕይወት ጉዞውን ትዕይንታዊ በሆነ ውብ ቋንቋ በመተረክ የትዝታ ብልጭታዎቹን (ከኢትዮጵያ እስከ አሜሪካ፣ ከልጅነት እስከ ጐልማሳነት) ሳይሰስት ያጋራናል።
Reviews
There are no reviews yet.