Cart

  • Home
  • Fiction

ዛሬ ቅዳሜ አይደለም Zare Kedame Aydelem by Natnael Kerealem

$20.00

ዛሬ ቅዳሜ አይደለም Zare Kedame Aydelem a book by Natnael Kerealem.

Addis Books!

August 5, 2024 Amharic

Authors

Meet the Author

Natnael Kerealem

Books By Natnael Kerealem View All
እውነት / አዛምድ Ewnet /Azamed by Natnael Kerealem
እውነት / አዛምድ Ewnet /Azamed by Natnael Kerealem
ትናንት እመጣለሁ Tenant Emetalehu by Natnael Kerealem
ትናንት እመጣለሁ Tenant Emetalehu by Natnael Kerealem
ዛሬ ቅዳሜ አይደለም Zare Kedame Aydelem by Natnael Kerealem
ዛሬ ቅዳሜ አይደለም Zare Kedame Aydelem by Natnael Kerealem

Description

ዛሬ ቅዳሜ አይደለም Zare Kedame Aydelem by Natnael Kerealem

ዕለተ ቅዳሜን ስለካደው መጽሐፍ

ዛሬ ቅዳሜ አይደለም ወሰን አልባ በሆኑ እና የገዛ ራሳቸውን ሁለንተና በተላበሱ እንዲሁም የተላበሱ በመሰሉ ተረኮች እና ጥያቄን አንስተው ነገር ግን አድምተው መልስ ሊሰጡ በሚሳናቸው (የተሳናቸው በመሰሉ) አንባቢን አብዝቶ ያሰላስል ዘንድ መንገድ አስይዘው በሚመለሱ ሸኚ ሀሳቦች (“ደራሲ ሁሉን ፈትፍቼ ላስረዳ ፣ እስከ ቤትህ ላድርስህ ካለ አንባቢውን ንቆታል ማለት ነው!” ይባል የለ) የተሞላ መጽሐፍ ነው፡፡

ታሪኮቹ በሕልም ዓለም ይፈጠር ስለሚሆን ውዝግብ እና የገጸ ባህርይ ራስን የመጠራጠር እና የማግኘት ግጭት እና ፍጭት ፣ የMythological እና Fantasy ቅርጽን በተላበሱ (ሊላበሱ በሞከሩ) ፣ ግዑዝ ያናግር ዘንድ አይቻለው በማይሆን ጤናማነቱን ከእርሱ በቀር ይገነዘበው ይኖር ስላልታደለ ገጸ ባህርይ ፣ ልጅ ስጦታ አይሆን ዘንድ ታምን ስለምትሆን እናት ፤ በሁኔታዎች መቀየር ይቀየር ሊሆን ስለሚታደል ወይም ስለሚበደል የውስጥ አቋም ፣ ከሞት በኋላ ይኖር ስለሚሆን የሚታሰብ ዓለም እና ሌሎችም ለመዳሰስ (ሸኚ ሀሳብ ለመስጠት) ተሞክሯል፡፡

በዘፈቀደ ሀሳቦቹ አይነሱ ይታሰቡ የሚሆኑ ፣ አንድ መሆኑን እንገነዘብ ዘንድ ይቸግረን በሚሆን ስም አልባ ገጸ ባህርይ ፍልስፍናዊ ፣ መለኮታዊ እንዲሁም ማኅበራዊ ሀሳቦች ይነሳሉ፡፡

 ከነባር የሥነ ጽሑፍ ሥርዓት ጋር በመዛመድ የራሳቸውን ቅርጽ እና ማንነት የማንፀባረቅ ኃይልን የሚታደሉ… በጊዜ ሂደትም ራሳቸው ከነባር የሥነ ጽሑፍ ሥርዓት ጋር በመመደብ እርስ በእርሳቸው መዛመድ የሚችሉ ነገር ግን የራሳቸውን ቅርጽ እና ማንነት የማንፀባረቅ ኃይልን የሚታደሉ ሌሎችን መፍጠር የሚችሉ መጽሐፍትን በየጊዜዉ ለማየት አንታደልም።

ይህን በቀደመ ሥርዓት ውስጥ መፈጠር የሚችል ነገር ግን ከተፈጠረበት አኗኗር በማፈንገጥ የራሱን ሁለንተና የሚፈጥር “ዛሬ ቅዳሜ አይደለም” የተሰኘ መጽሐፍ ለማንበብ ታደልኩ!

ፈጠራ በተሞላበት “Innovative storytelling technique” የለመድናቸውን የሥነ ጽሑፍ ሰበዞች ያልዳሰሰ ሊያስብል በሚቃጣ ነገርግን በተለየ መንገድ ስለዳሰሰ ፣ ጨርቁን በጣለ “ዕብድ” ይነገራሉ ወይም ይነሳሉ ተብለው የሚታሰቡ ስል ሀሳቦችን እጅግ በተዋዛ አንዳንዴም በፈጠጠ መንገድ በማቅረብ የተደራሲውን ልብ ሰቅዞ በመያዝ ስሙን እንኳን ከማናውቀው ገፀ ባህርይ እስከ መኖሩ የማይታወቅ “ጊዜ” ያለ ውስን “time frame” ነፃነቱን አውጆ ፣ ነፃነታችንን የሚያጎናጽፈንን ሥራ በተመለከትኩ ጊዜ እንደ መምህር ብቻ ሳይሆን እንደ አንድ መጽሐፍ ወዳድ ግለሰብ ተደስቻለሁ።

“የኢትዮጵያን ሥነ ጽሑፍ አንድ እርምጃ…” ፣ “የሀገራችን ሥነ ጽሁፍ ከፍ እያለ ስለመምጣቱ…” የሚሉ እና የመሳሰሉ ሀሳቦችን የዘነጋን መስለን በጊዜ ውስጥ እንዳሻን ወደፊት እና ወደኋላ እንዲሁም ወደታች እና ወደላይ እየተረማመድን የፈጠራ አጥር ይገፋ ስላልተሳነው መጽሐፍ ብቻዬን መስካሪ አልሆን ዘንድ ጠይቄያለሁ!
መልካም ንባብ!

“ዛሬ ቅዳሜ አይደለም”

ዮሴፍ ተመስገን (የቋንቋ እና ሥነ ጽሑፍ መምህር)

Reviews

There are no reviews yet.

Be the first to review “ዛሬ ቅዳሜ አይደለም Zare Kedame Aydelem by Natnael Kerealem”
AddisBooks Ads