Description
ዝሃ Zeha by Author Dagmawi Amelewerk
የደራሲዳግማዊ አመለወርቅ አዲሱ መጽሐፍ «ዝሃ» መጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም (ማርች 16, 2026) በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በታላቅ ድምቀት ተመርቋል፡፡
“ዝሃ” የአንድ ትውልድ “ምርቃት” ወይንም “ኑዛዜ” ነው፡፡ መጽሐፉ አንድን ቤተሰብ መሠረት አድርጎ የአገራችንን ያለፉት ስድሳ ሰባ ዓመታት ኩነታትን ለማጠናቀር ይሞክራል፡፡ ከልጅነት ዓይን ዕይታ በማንጸርና የታሪኩን አንጓ ከሃምሳ ዓመታት በፊት በተፈጠረው ሕዝባዊ ንቅናቄ ሳቢያ እንደበረሮ የተጨፈለቀን ቤተሰብ ማዕከል በማድረግ፤ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ለምን የተለያዩ የአስተሳሰብ፣ የአመለካከትና የዝንባሌ ልዩነቶችን ሊያሳይ ቻለ ብሎ ያጠይቃል፡፡ ከዚያ በኋላ የተፈጠረው ቀጣይ ትውልድ ዕለት ተዕለት “ደም ማየት” ዕጣ ፈንታው ለምን ሆነ ብሎ ሊመረምርና ሊያሳይ ይሞክራል፡፡ የልጅነትን ውስጣዊ ቁስልና ጉዳት በማሳየት ከዚያም ጋር ተያይዘው የመጡ ስነልቡናዊ፣ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶችን ያስቃኛል፡፡ በስተመጨረሻ እንዴትስ በይቅርታ በንስሀ መጓዝ አለብን የሚሉ ኮርኳሪ ጥያቄዎችን ያነሳል፡፡
Reviews (0)
You must be logged in to post a review.
AddisBooks Ads



Reviews
There are no reviews yet.