ፍካሬ: Fikarie by Alemayehu Wassie
ከመጽሃፉ የተወሰደ " ለዚህ ሁሉ ጭቅጭቅና መከራ የተዳረግነው በዚህ ጫካ
መኖራችን ነው። ሲጀመር ይሄ ጫካ ለእኛ ምን ጠቀመን? የባሰ
እስር ቤት ነው የሆነብን! ዓይነታችን በዝቶ አንዳችን በሌላችን
ተጭነን፣ የመታፈን ጭንቀት እንጅ የነፃነት ስሜት የለንም።
እና ይሄ ጫካ ለእኔ ምኔ ነው!’ አለ ።
ይሄንን ተከትለው እነ ቆንጥርና አጣጥ ተንጣጡ።
‘አዎ! ጫካ የሚለውን ቃል ራሱ መስማት ሰልችቶናል!’ አሉ
በዚህን ጊዜ፡-
‘እና ምን ይሁን ነው የምትሉት?’ አለ ጭንቅ ብሎት ‹ላሎ›።
ላሎ የሚባለው ዛፍ እንዲህ ያለ ጨከን ያለ ነገር አይወድም።
እንኳንስ ከዛፍና ከቁጥቋጦ ጋር ከሰው ልጅ ሰብሎች ከሆኑት
ከማሽላና ዘንጋዳ ጋር በፍቅር የሚኖር ነው። የሰው ልጅም፡-
‹ላሎዬ ላሎዬ፣ አኻይ ላሎ ላሎ› "
Publisher : EnjeraPress
Publication date : September 9, 2025
Language : Afrikaans
Print length : 202 pages
ISBN-10 : 1969702079
ISBN-13 : 978-1969702075
Item Weight : 12.8 ounces
Dimensions : 6 x 0.46 x 9 inches
Best Sellers Rank: #296,737 in Books (See Top 100 in Books) #6,653 in Classic Literature & Fiction #10,454 in Literary Fiction (Books)
$27.65
ሚተራሊዮን: Miteralion
ሚተራሊዮን: Miteralion book by Dr.Alemayehu Wassie Eshete
ከመጽሃፉ የተወሰደ ...." አንድ ሁለት መቶ ሜትር እንደተጓዙ አንድ ጫማ በላይ በአንድ ጊዜ
የማታስረግጥ የበሬ ምላስ የምታክል የሠርጥ መንገድ ተከትለው
መውረድ ጀመሩ፡፡ በግራ በኩል ጭው ያለ ገደል በቀኝ በኩል ደግሞ
የሚያዝ የሚጨበጥ የሌለው ዐለት ከመንገዱ ጥበትና ተዳፋትነቱ
ተጨማምሮ “‹ወደ ጽድቅ የሚወስደው መንገድ ጠባብ ነው› የተባለው
ይሄ ይሆን?” አልኩ፡፡ ትንሽ እንደተራመድን ለመውረድ ሰውነቴ
ሲንቀጠቀጥ " ….
….. "አባ መዐዛ መንገድ ላይ ስንመጣ ስለ ኢነርጂ ዲስፔሽን የጠየቀኝ ትዝ
አለኛና ‹ይሄ ሰው ስለዚህ ስፍራ ቀደም ብሎ መረጃ ነበረው ማለት
ነው? እነዚያ ቦታዎችም ማስተንፈሻ ናቸው ማለት ነው?› አልኩ
ለራሴ ….."
$29.99
እመጓ: Emegua by Dr.Alemayehu Wassie
ከመጽሃፉ የተወሰደ "በቅዱሱ ዋሻ ውስጥ ምን እንደደረሰብኝ ቁልጭ ብሎ
ታወሰኝ። ከጨለማው ክፍል በፍጥነት ወጥቼ በወርቃማ ጥልፍ
ሥዕል ያማረውን ሐምራዊ መጋረጃ ጫፉን በእጄ አጥብቄ ይዤ
ከታች ወደ ላይ ከቀኝ ወደ ግራ በፍጥነት ገለጥ ሳደርገው ድንገት
ምንነቱን ያላወቅሁት የብርሃን ጎርፍ ከአስደንጋጭ መብረቃዊ ኃይል
ጋር ተጣምሮ ወደ ላይ አንሥቶ ማዶ ካለው የዋሻ ቋጥኝ ጋር
አላተመኝ። ድንጋጤና ከባድ ሕመም ተዳምረው ወዲያው ራሴን
አሳቱኝ። ከዚያ በኋላ የሆነውን የማስታውሰው ነገር አይደለም።
በመጨረሻ አሁን በእማሆይ ዕሴተ ማርያም አስታማሚነት ራሴን
ሞላሌ ጤና ጣቢያ አገኘሁት። “አለመሞቴ ተመስገን ነው!” አልኩና
እንባዬን መጠራረግ ጀመርሁ። "
Publisher : EnjeraPress
Publication date : September 7, 2025
Language : Afrikaans
Print length : 206 pages
ISBN-10 : 1969702001
ISBN-13 : 978-1969702006
Item Weight : 13.1 ounces
Dimensions : 6 x 0.47 x 9 inches
Best Sellers Rank: #885,547 in Books (See Top 100 in Books) #9,670 in Action & Adventure Fantasy (Books) #15,074 in Classic Literature & Fiction #18,390 in Memoirs (Books)
$29.99






