🌟 የመፅሐፍ ምረቃ ጥሪ 🌟
“ለምን?” የለውጥ መጀመሪያ ጥያቄ !
በደራሲ አዱኛ ሂርጳ የተፃፈውና “አለመቻልን የምትፋለመው ትንሿ ጠጠር” በሚል ንዑስ ርዕስ የሚታወቀው “ለምን?” የተሰኘው አዲስ መፅሐፍ የፊታችን ቅዳሜ በድምቀት ይመረቃል። የዚህ ልዩ መርሀ ግብር አካል እንዲሆኑ ተጋብዘዋል።
📅 ቀን፦ ቅዳሜ፣ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም
🕙 ሰዓት፦ ከቀኑ 10፡30 ጀምሮ
📍 ቦታ፦ ወዳጅነት ፓርክ (Friendship Park)፣ አዲስ አበባ
በዕለቱ የሚጠበቁ የክብር እንግዶች እና ተናጋሪዎች፦
- ክብርት አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን
- አቶ ሺፈራው ወልደሚካኤል (የቀድሞ የፍትህ ሚኒስትር)
- ዶክተር ምህረት ደበበ
- አቶ ክብረት አበበ (የጠብታ አምቡላንስ መሥራች)
የመፅሐፍ ቅኝት የሚያቀርቡ፦
- ቢንያም አቡራ
- ደራሲ መሐመድ አል ቡርሀን
የመድረክ አጋፋሪ፦
- ገጣሚ ረድኤት ተረፈ
የጥበብና የእውቀት ማዕድ በሆነው በዚህ የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ በመገኘት የደራሲውን አዲስ ስራ አብረን እንመርቃለን።