“ሀገር እና ዓድዋ”
ዋልያ የሐሳብ እና መጻሕፍት መድረክ
ስለ ሀገራችን ማወቅ ያሉብንን እውነታዎች ምንድናቸው? እነሱንስ የምንገልጽባቸውን ወሳኝ ቃላት ምን ያህል እንግባባ’ባቸዋለን? ስሞችን በትክክል ካላወቅን ወይም የጋራ ስም ካልፈጠርን ለጋራ ሀገር በጋራ መሰለፋችንን እርግጠኛ መሆን ይቻላል ወይ?
ሀገር፣ ድንበር ፣ መንግሥት፣ ሕዝብ፣ ሉዓላዊነት ፣ ዜጋ፣ ጦርነት ፣ ወዘተ የሚሉ ስሞች ላይ የፖለቲካ፣ የታሪክ እና የሕግ ትንታኔ እንዲያቀርቡ ምሁራንን ጋብዘናል። ኑና ሀሳብ ተካፈሉ፣ አካፍሉ።
አወያይ:-
ፍሬው ማዕሩፍ
/ከ ሕግ ፍልስፍና/
አቅራቢዎች:-
ፕሮፌሰር አህመድ ዘከሪያ
/ከታሪክ አንፃር/
ፕሮፌሰር ብሩክ ኃይሉ
/ከፖለቲካ አንፃር/
የሕግ ባለሙያ አንዱዓለም በዕውቀቱ
/ከሕግ አንፃር/
ቀን: ቅዳሜ የካቲት 21 – ከቀኑ 8:30 ጀምሮ
ቦታ : አራት ኪሎ ዋልያ አዳራሽ – ኢክላስ ሕንጻ 4ኛ ፎቅ
ቅዳሜ ከሰዓትዎን የዓድዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ ባዘጋጀነው ልዩ ፕሮግራም ያሳልፉ!