Loading Events

የሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅን 20ኛ ዓመት የዕረፍት መታሰቢያ ዝግጅት

የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ ሥነ ጥበባት ማዕከል፣ የሎሬት ጸጋዬ ገ/መድኅንን 20ኛ ዓመት የዕረፍት መታሰቢያ ዝግጅት የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 14፣ 2018 ዓ.ም ከ8፡00 ሰዓት ጀምሮ ያካሄዳል፡፡

በዝግጅቱ ላይ አቶ ነብዩ ባዬ (በአ.አ.ዩ የቴአትር ጥበባት ት/ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር) – የጸጋዬን ቴአትሮች ይዳስሳል፣ አቶ ወንድወሰን አዳነ (የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሥነጽሑፍ መምህር ረዳት ፕሮፌሰር) ግጥሞቹን ይተነትናል፣ የሥነ ጽሑፍ ኀያሲው ቴዎድሮስ አጥላው በጸጋዬ ሕይወት ዙሪያ የተጻፈውን ‹‹ምጥቀት በቅኔ አክናፍ›› የተሰኘውን መጽሐፍ ይዳሰሳል፡፡

በዝግጅቱ ላይ ሁሉም እንዲታደም የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ ሥነ ጥበባት ከወዲሁ ግብዣውን ያቀርባል፡፡

አድራሻ፡- የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ቅጥር ግቢ (ጳውሎስ ሆስፒታል አካባቢ) ንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ አለፍ እንዳሉ ጠቋሚውን ያገኙታል

Tsegaye Gebremedhin 20th anniversary

Tsegaye Gabremedhin (1936–2006) was an Ethiopian playwright and poet who wrote in Amharic and English.

He was director of the Haile Selassie I Theatre (now the Ethiopian National Theatre) from 1961 to 1971. He later founded the theatre department at Addis Ababa University.

Tsegaye wrote more than 30 plays, most of them in Amharic, and translated several plays by William Shakespeare and Molière. His Amharic plays deal primarily with contemporary Ethiopia, in particular the plight of youth in the cities and the need to respect traditional morality, as in Crown of Thorns (1959). Oda Oak Oracle (1965) is Tsegaye’s best-known verse drama in English. Like his other English-language plays, it is based on Ethiopian history and deals with religious conflicts. Collision of Altars (1977) is an experimental play that incorporates pantomime, incantation, dance and the use of masks.

 

Location

Location
The Ethiopian Academy of Sciences
Address
https://maps.app.goo.gl/d2Tp7dY63y8Nv1jj7
Addis Ababa, Addis Ababa Ethiopia

Leave a Reply