የክብር ግብዣ፡ “የቼቼላው አባታችን” የመጽሐፍ ምረቃ!
ለግማሽ ክፍለ ዘመን (ለ52 ዓመታት) በሕክምናው ዘርፍ በቅንነትና በታማኝነት በማገልገል፣ አያሌ ፕሮፌሰሮችንና ዶክተሮችን ያፈሩት የኢትዮጵያ ባለውለታ ፕ/ር ማለደ ማሩ የሕይወት ታሪክ አሁን በታተመ መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል።
በአስተባባሪ ኮሚቴዎች እገዛ፣ በታታሪው ደራሲ ዶ/ር ሰሎሞን በርሄ የተሰናዳውና የባለውለታውን አሻራ የሚዘክረው ❝የቼቼላው አባታችን❞ የተሰኘው መጽሐፍ በደመቀ ሁኔታ ይመረቃል።
በዕለቱ የሚገኙ የክብር እንግዶች፦
ፕሮፌሰር ማለደ ማሩ (የመጽሐፉ ባለታሪክ)
ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ (ተናጋሪ)
ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ (ተናጋሪ)
ዶ/ር ሰሎሞን በርሄ (የመጽሐፉ ደራሲ)
የመጽሐፉ አዘጋጅ ኮሚቴ አባላት
የምረቃው መርሃ-ግብር፦
ቀን፦ ቅዳሜ፣ መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም
ሰዓት፦ ከቀኑ 8:00 ጀምሮ
ቦታ፦ ቀበና አደባባይ በሚገኘው የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ማህበር (EPHA) አዳራሽ
ታላላቅ የሕክምና ባለሙያዎች፣ የሀገር ባለውለታዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በሚገኙበት በዚህ ታሪካዊ መርሃ-ግብር ላይ እንዲገኙ በክብር ተጋብዘዋል።
መግቢያው በነጻ ነው!
ኢትዮጵያ ባለውለታዎቿን ታከብራለች! በዕለቱ እንገናኝ።
AddisBooks Ads