Autobiography - Addis Books https://addisbooks.com Ethiopian Books and Authors Fri, 19 Jun 2026 07:41:40 +0000 en-US hourly 1 https://wordpress.org/?v=7.0.3 https://addisbooks.com/wp-content/uploads/2023/12/cropped-cropped-addisbooks-logo-1-32x32.png Autobiography - Addis Books https://addisbooks.com 32 32 Sew Bertu Beret Kentu ሰው ብርቱ ብረት ከንቱ by Tilahun Fanta https://addisbooks.com/book/sew-bertu-beret-kentu-by-tilahun-fanta/ https://addisbooks.com/book/sew-bertu-beret-kentu-by-tilahun-fanta/#respond Thu, 18 Jun 2026 20:25:33 +0000 https://addisbooks.com/?post_type=product&p=7043 Sew Bertu Beret Kentu ሰው ብርቱ ብረት ከንቱ by Tilahun Fanta .

Addis Books!

The post Sew Bertu Beret Kentu ሰው ብርቱ ብረት ከንቱ by Tilahun Fanta first appeared on Addis Books.

]]>
Sew Bertu Beret Kentu ሰው ብርቱ ብረት ከንቱ by Tilahun Fanta 

አሪፍ ታሪክ ነጋሪ፥ ወግ አጋሪ፥ ከራስ ጋር አነጋጋሪ መጽሃፍ ነው። በጨዋታ ለዛ የማህበራዊ ሂስ አቀራረቡ ልብ አይቆረቁሬ ነው። መጽሃፉ አንኳር የአገራችንን ችግሮች የተንጸባረቀበት ነው። ስለትምህርት ጥራት፥ ስለሙያ እውቀት አስፈላጊነት እና ፈተናው፥ ስለ ባላገሩ ኑሮ ምስል፥ ስለ ፖለቲካችን ገመና፥ አማራው በሽግግር ዘመን ከክልሉ ውጪ ስላየው፥ አበሳ፥ ስለንግድ እና የንግድ ፈቃድ ስንክሳር፥ ስለህዝባችን የ’ምትሃት’ መፍትሄ ፈላጊነት  ምኑ ቅጡ! ደራሲው ከረገጠው መሬት ሁሉ እግሩ ወርቅ ይዞ ነው የተነሳው።

አባ ታድያ አለንጋቸው አይጣልባችሁ፤የልጅ ፍቅር ጌታ የሰጣቸው አይመስለኝም፡፡ ላለመገረፍ ጎንበስ ብሎ ጫማ መሳም፣ መስቀል መሳለም፣ ወጥቶ ፊደል ማስቆጠር ዋናዎቹ ነበሩና ሁሉንም ፈጽሜ ከዛ አለንጋቸው ለማምለጥ በጠዋቱ ነበር ጥረቴን የጀመርኩት፡፡

በሦስት ወር ገደማ እግዚአብሔር ራሱን በአልፋ ጀምሮ በኦሜጋ እንዲጨርስ አባም በሚያስተምሩበት ዘይቤ ፊደልን ከሀ – ፖ ለየሁ፡፡ ማንና ማን እንደወለዷቸው ሳላውቅ ዲቃላ ፊደላት የምትሏቸውንም አወቅኋቸው፡፡ ቁጥርን በግዕዙም በፈረንጁም ለመድኩት፡፡

አባ ፈለገ ሰይጣን ከመጣና ካጣላን እንደማያስተርፉኝ አውቄ ሁሌ በጥንቃቄ ብማርም ቀኔ ደረሰችና ፊደል እንዳስቆጥር ጥግ ሆነው እግራቸውን አንፈራጠው ጭራቸውን እያወዛወዙ ተነሥ ሲሉኝ እንደሌላው ቀን ኮራ እንዳልኩ ወጥቼ

“ሀ – ግዕዝ” ስል ቤቱን የሞላው ተማሪ ደስ በሚል ቅላጼ “ሀ – ግዕዝ” ብለው ተከተሉኝ፡፡

ሁ – ካብዕ
ሂ – ሳልስ
ሃ – ራብዕ
ሄ – ሐምስ
ህ – ሳድስ

ሆ – ሳ ብ ዕ እያልኩ የመጀመርያ መስመሩን አስቆጠርኩ፡፡ ሁለተኛውን መስመር ጀምሬ

ለ – ግዕዝ
ሉ – ካብእ
ሊ- ሳልስ
ላ – ራብዕ

እንዳልኩ ያልጠበኩት ነገር ተፈጠረ፡፡ ከፊደሉ ጀርባ ያለው የአፈር ቤት ግድግዳ ከኋላ የተሰነጠቀ ነበርና አባ አዲስ የገዙት ፊደል ማስቆጠርያ “ላ” ፊደልን በጣም ተጭኜአት ኖሮ ግድግዳው ውስጥ ሰምጣ ቀረች፡፡

ከመቅጽበት ትንሸዋ ልቤ ደለቀች፡፡ በድንጋጤ እኔ ሌ- ሐምስ ባልልም ተማሪው በልምድ ሌ- ሐምስ በማለት እየቆጠረ ነበር፡፡ አባ ሁኔታውን ከማስተዋላቸው በፊት ማስቆጠሪያ ዱላዬን በአየር ላይ ለቅቄ ከቄስ ትምህርት ቤቱ በሩጫ ወጥቼ ንፋስ በጆሮዬ እያፏጨ ቤት ደረስኩ፡፡ እናቴ በሁኔታዬ ተገርማ ምን እንደተፈጠረ ሳትጠይቀኝ በፊት ለፈለፍኩ፡፡

እናቴ በዚህ ሁኔታ በነጋታው ከመለሰችኝ እንደማያስተርፉኝ ስለገባት ሳምንት ቆየችና አሁን ይረሳሉ ወይም ይራራሉ በማለት “ፊደል እገዛለሁ እንጂ ከጓደኞችህ ተለይተህ ሳትማር እንዴት ትቀራለህ ?” ብላ የወር ክፍያውን አንድ ብር ይዛ እኔን አስከትላ እሷ ፈራ ተባ እያለች እኔም እየተንቀጠቀጥኩ አባ ዘንድ ቀረብን፡፡
…….

The post Sew Bertu Beret Kentu ሰው ብርቱ ብረት ከንቱ by Tilahun Fanta first appeared on Addis Books.

]]>
https://addisbooks.com/book/sew-bertu-beret-kentu-by-tilahun-fanta/feed/ 0
My Poems and Memory Notes ግጥሞቼና ትዝታዎቼ by Fekadu Fullas https://addisbooks.com/book/my-poems-and-memory-notes-by-fekadu-fullas/ https://addisbooks.com/book/my-poems-and-memory-notes-by-fekadu-fullas/#respond Mon, 20 Apr 2026 11:17:22 +0000 https://addisbooks.com/?post_type=product&p=6524 My Poems and Memory Notes ግጥሞቼና ትዝታዎቼ  by Fekadu Fullas

 

The post My Poems and Memory Notes ግጥሞቼና ትዝታዎቼ by Fekadu Fullas first appeared on Addis Books.

]]>
My Poems and Memory Notes ግጥሞቼና ትዝታዎቼ  by Fekadu Fullas

The book is an anthology of poems and short stories based on my childhood, adulthood, and professional life experiences. The book has three sections: Amharic poems, English poems, and short stories based on my life experiences.

The post My Poems and Memory Notes ግጥሞቼና ትዝታዎቼ by Fekadu Fullas first appeared on Addis Books.

]]>
https://addisbooks.com/book/my-poems-and-memory-notes-by-fekadu-fullas/feed/ 0
Autobiography, Poems, and Scientific Articles by Fekadu Fullas https://addisbooks.com/book/autobiography-poems-and-scientific-articles-by-fekadu-fullas/ https://addisbooks.com/book/autobiography-poems-and-scientific-articles-by-fekadu-fullas/#respond Wed, 15 Apr 2026 22:24:05 +0000 https://addisbooks.com/?post_type=product&p=6487 Autobiography, Poems, and Scientific Articles by Dr. Fekadu Fullas

The post Autobiography, Poems, and Scientific Articles by Fekadu Fullas first appeared on Addis Books.

]]>
Autobiography, Poems, and Scientific Articles by Fekadu Fullas

 

The book is a hybrid of autobiography, poems (in both English and the Ethiopian vernacular, Amharic), and a collection of articles on Ethiopian medicinal plants. The bulk of the book is on my childhood and adult experiences while growing up in Addis Ababa, Ethiopia, and later during my academic life in the USA. Keeping a diary was uncommon, especially when I was growing up; therefore, I had to rely on my memory to reconstruct events from various periods of my life. Although I had a predisposition to language both in the colloquial and literary sense, I didn’t try my hands on this aspect early in life.

In a previous and current book, I wanted to experiment with poetry pieces which capture my feelings about Nature and other experiences. In addition, apart from writing in mainstream scientific academic journals, I used to pen popular articles on medicinal plants and share them on social media platforms and among discussion groups. A sampling of those articles is also included in this book.
The book is divided into four main parts. Part 1 focuses on my upbringing and is sprinkled with the most memorable life events, at least to me. This part covers my traditional and early modern school years and extends a little into my college years. It also discusses the latter part of my life in the USA as a doctoral student in the early 80’s and a post-doctoral researcher in the early 90’s.

Part 2 delves into poetic eruptions written in the Ethiopian vernacular Amharic, that were drawn from sentimental experiences, be it from just observing Nature or reading and hearing about important events both in Ethiopia and elsewhere. The same poetic lava flows into Part 3 with a similar genre but penned in English. The last part of the book, Part 4, is a collection of selected articles that I wrote at various times in newspapers, on social media, and for discussion groups. They focus mainly on Ethiopian medicinal plants.

This author believes that there are certain sections that may appeal to interested readers. Some readers may relate to the stories told in the book. Those who are inclined to poetry may share similar sentiments expressed in the poems. Other readers who are science-minded can also extract some information from the book.

The post Autobiography, Poems, and Scientific Articles by Fekadu Fullas first appeared on Addis Books.

]]>
https://addisbooks.com/book/autobiography-poems-and-scientific-articles-by-fekadu-fullas/feed/ 0
ዮዲታ Yodita by Roman Tewolde https://addisbooks.com/book/yodita-by-roman-tewolde/ https://addisbooks.com/book/yodita-by-roman-tewolde/#respond Fri, 27 Feb 2026 13:13:06 +0000 https://addisbooks.com/?post_type=product&p=5980 ዮዲታ Yodita, a book by Roman Tewolde.
Addis Books!

The post ዮዲታ Yodita by Roman Tewolde first appeared on Addis Books.

]]>
ዮዲታ በሮማን ተወልደ
ዮዲታ(Yodita) በሮማን ተወልደብርሃን ገብረእግዚአብሔር የተጻፈና በቅርቡ በታህሳስ ወር 2018 (እ.ኤ.አ. ኖቬምበር 2025) ለንባብ የበቃ የግለ-ታሪክ (Autobiography) መጽሐፍ ነው። 

የመጽሐፉ ዋና ዋና ነጥቦች፦

  • ይዘት፦ ደራሲዋ ያደገችበትን የቤተሰብ ታሪክ፣ የልጅነት ትውስታዎቿን እና በሕይወቷ ላይ ተጽዕኖ ያሳደሩ ክስተቶችን ይተርካል። በተለይም በ1980ዎቹ መጨረሻ እና በ1990ዎቹ መጀመሪያ በአሥመራ ከተማ የነበረውን ሁኔታ በልጅ ዓይን ያሳያል።
  • ርዕስ፦ “ዮዲታ” የሚለው ርዕስ የተሰጠው ደራሲዋ ከክርስትና እናቷ ባገኘችው ሁለተኛ ስሟ እንደሆነ ተገልጿል።
  • ቤተሰባዊ ዳራ፦ ሮማን የታወቁት የአካባቢ ጥበቃ ሳይንቲስት የዶክተር ተወልደብርሃን ገብረእግዚአብሔር እና የሱ ኤድዋርድስ ልጅ ስትሆን፣ መጽሐፉ እንደ ደራሲ ስብሃት ገብረእግዚአብሔር ያሉ የቅርብ ዘመዶቿንም ታሪክ ይዳስሳል።
  • ምረቃ፦ መጽሐፉ በታህሳስ ወር 2018 ዓ.ም (ዲሴምበር 2025) በአዲስ አበባ ጃፋር መጽሐፍት መደብር ተመርቋል።

The post ዮዲታ Yodita by Roman Tewolde first appeared on Addis Books.

]]>
https://addisbooks.com/book/yodita-by-roman-tewolde/feed/ 0
Endihem Tenurual by Abera Lemma  https://addisbooks.com/book/endihem-tenurual-by-abera-lemma/ https://addisbooks.com/book/endihem-tenurual-by-abera-lemma/#respond Wed, 11 Feb 2026 16:01:14 +0000 https://addisbooks.com/?post_type=product&p=5126 እንዲህም ተኑሯል Endihem Tenurual a book by Abera Lemma.

የደራሲና ጋዜጠኛ አበራ ለማ ግለ ታሪክ መጽሃፍ በዝነኛው የከተማችን ዘመናዊ የመጽሃፍ መደብር መሸጫ በሆነው በሁሉም የጃዕፈር መጽሃፍት መደብሮች ከቅዳሜ ጥር 23, 2018 ዓ/ም ማግኘት እንችላለን።

The post Endihem Tenurual by Abera Lemma  first appeared on Addis Books.

]]>
እንዲህም ተኑሯል Endihem Tenurual by Abera Lemma 

ከ1966 ዓ/ም አብዮቱ ከፈነዳበት ማግስት ጀምሮ እስከ ዛሬው የግለ ታሪኩ መጽሃፊ ድረስ ከ21 ያላነሱ የግጥም መድብሎችንና አጫጭር ልቦለዶችን በመፃፍ በአንባቢያን ዘንድ ከፍ ያለ ክብርን ያገኘው አንጋፋው ደራሲ : ገጣሚና ጋዜጠኛ አበራ ለማ የራሱን ግለታሪክ “እንዲህም ተኑሯል” የሚል ርዕስ ጽፎ የተዘጋጀውን መጽሃፍ የካቲት 7, 2018 ዓ.ም በወመዘክር ኅሩይ አዳራሽ የተለያዬ ደራሲያን : ተጋባዥ እንግዶች : የደራሲው ቤተሰብ ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት በክብር የሚመረቅ ሲሆን ይህ የደራሲው ግለ ታሪክ መጽሃፍ ለታዳሚው የዳሰሳ ፅሑፍ ከሌሎች ፕሮግራሞች ጋር የሚቀርብ ይሆናል።

ጋዜጠኛ ደራሲ አበራ ለማ በህይወት ዘመኑ በስነጽሁፊ ዘርፍ : በግል ህይዎቱ : በጋዜጠኝነት ሙያው : በኢትዮጵያ በነበሩ የፓለቲካ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ የነበረው ተሞክሮ እውቀት እና ልምድ ለትውልዱ በግለ ታሪኩ ሊያሳውቀን ሊያስተምረን እንዲህም ተኑሯል በሚል ያሳተመውን ግለታሪክ መጽሃፍ በመግዛት ለደራሲና ጋዜጠኛ አበራ ለማ ያለንን ፍቅር አክብሮት እንግለጽለት ።

ይህንን የደራሲና ጋዜጠኛ አበራ ለማ ግለ ታሪክ መጽሃፍ በዝነኛው የከተማችን ዘመናዊ የመጽሃፍ መደብር መሸጫ በሆነው በሁሉም የጃዕፈር መጽሃፍት መደብሮች ከቅዳሜ ጥር 23, 2018 ዓ/ም ማግኘት እንችላለን።

ጋዜጠኛ ደራሲ አበራ ለማ

“…እንዲህም ተኑሯል” የሚል ርዕስ ያለው በ550 ገፆች የተሰናዳው የደራሲና ጋዜጠኛ አበራ ለማ የሕይወት ታሪክ ምረቃ ቅዳሜ የካቲት 14 2018 ዓ.ም በወመዘክር ኅሩይ አዳራሽ ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።
በዕለቱ፣ ታላላቅ እንግዶች በተናጋሪነት የሚጋበዙ ሲሆን በግለ -ታሪክ መፅሀፉም ላይ የዳሰሳ ፅሑፍ ይቀርባል።
አበራ ለማ፣ ካገራችን ገጣሚያንና አጫጭር ልብ-ወለድ ጸሓፊዎች አንዱ ሲሆን በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነፅሑፍ ጥናት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂም፣ ነው።
አበራ፣ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ፕሬስ መምሪያዎች ሠርቷል። ከጦር ግንባር ጋዜጠኝነት እስከ ኪነ-ጥበባት ዘርፎች ሀያሲነት የዘለቀ ሲሆን በአንባቢያን ተወዳጅ የሆኑ ሥራዎችንም ለማስነበብ የቻለ ነው።
ከአበራ ለማ የታተሙ ሥራዎች የሚከተሉት ይጠቀሳሉ።
1967 ኩል ወይስ ጥላሸት፣ የግጥም መድብል፣
1974 ሽበት፣የግጥም መድብል፣
1975 ሕይወትና ሞት፣የአጫጭር ልቦለዶች መድብል፣
1976 ሞገደኛው ነውጤ፣ ኖቭሌት፣
1978 አባደፋር፣ከሌሎች ደራስያን ጋር… ስብስብ፣
1978 ጽጌረዳ ብእር፣ከሌሎች ገጣሚያን ጋር… ስብስብ፣ እና ሌሎችንም ከ21 በላይ መፅሐፍትን ፅፎ ለማስነበብ በቅቷል።
የዚህ መርሐ ግብር የክብር እንግዳ ዶክተር ኃይሉ አርአያ ሲሆኑ ከተናጋሪዎች መካከልም እመቤት ሆይ ፍሬአለም ሺባባው እና ኢንጂነር ቢጃይ ናይከር ይገኙበታል።

The post Endihem Tenurual by Abera Lemma  first appeared on Addis Books.

]]>
https://addisbooks.com/book/endihem-tenurual-by-abera-lemma/feed/ 0
Kelijinet eske lijunet by Zeritu Kebede https://addisbooks.com/book/kelijinet-eske-lijunet-by-zeritu-kebede/ https://addisbooks.com/book/kelijinet-eske-lijunet-by-zeritu-kebede/#respond Tue, 10 Feb 2026 06:27:26 +0000 https://addisbooks.com/?post_type=product&p=5035 ከልጅነት እስከ ልጁነት kelijinet eske lijunet a book by Zeritu Kebede.

Addis Books!

The post Kelijinet eske lijunet by Zeritu Kebede first appeared on Addis Books.

]]>
ሁለገብ አርቲስት ዘሪቱ ከበደ በዜማዎቿና በትወናዎቿ ስታስደምመን ቆይታ፣ አሁን ደግሞ በብዕሯ አዲስ ድንቅ ስራ ይዛልን ቀርባለች። የመጀመሪያ ስራዋ የሆነውና በብዙዎች ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ከልጅነት እስከ ልጁነት የተሰኘው መፅሐፍ አሁን ለንባብ በቅቷል።

ይህ መፅሐፍ በውስጡ ምን ይዟል?

የህይወት ጉዞ፦ አርቲስቷ ካለፈችባቸው የተለያዩ የህይወት ውጣ ውረዶችና ልምዶች የተቀዳ።
መንፈሳዊ እይታ፦ ከስሙ መረዳት እንደሚቻለው “ከልጅነት” ወደ “ልጁነት” (ወደ ልጅነት ክብር) የተደረገን ጥልቅ መንፈሳዊና ስነ-ልቦናዊ ሽግግር የሚዳስስ።
ጥበብና ፍልስፍና፦ በዘሪቱ ልዩ የአጻጻፍ ስልት የተቃኘ፣ ለንባብ የሚማርክና ለህይወት አዲስ እይታን የሚሰጥ።

መፅሐፉን የት ያገኙታል?

• በሁሉም ዋና ዋና የመፅሐፍት መደብሮች።
• በተለይም በጃፋር መፅሐፍት መደብር እና በሌሎች ታዋቂ አከፋፋዮች ዘንድ ይገኛል።

የጥበብ አድማስዎን የሚያሰፋ፣ በሀሳብ የሚያረካና ለነፍስዎ ምግብ የሚሆን ድንቅ ስራ ስለሆነ ሳይረፍዱ የእርሶን ኮፒ ይግዙ።

 

The post Kelijinet eske lijunet by Zeritu Kebede first appeared on Addis Books.

]]>
https://addisbooks.com/book/kelijinet-eske-lijunet-by-zeritu-kebede/feed/ 0
መመለስ ቦጌ ትውስታዎቼ Memeles by Birtukan Mideksa https://addisbooks.com/book/memeles-birtukan-mideksa/ https://addisbooks.com/book/memeles-birtukan-mideksa/#respond Fri, 30 Jan 2026 17:20:41 +0000 https://addisbooks.com/?post_type=product&p=4686 Memeles A book by Birtukan Midekssa. Boge Tewestawoche - መመለስ ቦጌ ትውስታዎቼ

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በአቋም ጽናትና በአመራር ብቃቷ በምትታወቀው ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የተዘጋጀው "መመለስ፦ ቦጌ ትውስታዎቼ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል። ብርቱካን ሚደቅሳ በዚህ መጽሐፏ ታሪኳን የተረከችበት፣ ልምዷን ያካፈለችበት፣አስገራሚውን የሕይወት ታሪኳን አጋርታናለች።

Memeles book by Birtukan Midekssa

The post መመለስ ቦጌ ትውስታዎቼ Memeles by Birtukan Mideksa first appeared on Addis Books.

]]>
… የመጻፍ ሂደቴ ደጋግሞ እየወሰደኝ ያለው … እገሌ ወደተባልኩባቸው፣ ወደ አደባባይ ማንነቶቼ አልሆነም። ገና አንቱ ሳልባል፣ ከገባኝ በላይ በሆነ የመወደድ ብርሃን ዐቅፎ አኑሮኝ፣ ለፍትሕ እንድፀንስ፣ ለሀገር መውደድ እንድፈግግ ወዳደረገኝ ወደዛ የመውጫ ቤቴ (መንደሬ ወይም ሰፈሬ ስለው ያንስብኛል) እንደገና፣ እንደገና ይመልሰኝ ጀመር። ጨረስኩ ስል ሌላ ታሪክ… አበቃ ስል ሌላ ንሸጣ …

ነገር ግን ይህን መጽሐፍ አስቀድሜ በማምጣት የአደባባይ ታሪኬ ለኅትመት እስኪበቃ (እሱ የሚቀር ነገር አይደለም) በዚህ አዝግሙ ማለቴም አይደለም፤ በፍጹም። ይልቁንም የአደባባይ ሆነ የግል፣ የወጣትነት ሆነ የጎልማሳነት እውነቶቼ ሁሉ አውራ የሆነው ዋና እውነቴ ይሄኛው መሆኑን በትሕትና ማሳየቴ እንጂ።

… ሳጠቃልለው በአጭሩ ግለጪያት ብትሉኝ መመለስ ብዙ ፍቅር እና ብርሃን ለሰጠኝ ማኅበረሰብ (ቤቴ) ለበጎነቷ የጽሑፍ ሐውልት አቁሞ ብድሯን ስለመመለስ ነች – መልሼ የምጨርሰው ባይሆንም። ደግሞም ጫጩቷ መታቀፍን እና ሙቀትን ፈልጋ ወደ እናቷ ጉያ እንደምትሮጠው ዓይነት፣ ከመከራ ጋ ተሞካክረን ባበቃንበት ጊዜያት ሁሉ ወደ ቤቴ ስለ መመለስ፣ ስለ መመላለስም ነች። በመጠኑ ደሞ ከጸለምተኛ ዘመኖቼ በጥረት ወደ ቀድሞ ጥንካሬ ስለመመለስ (resilience)። እያዋዛች ለእናንተ ሌላ፣ ሌላም ትርጉም የመስጠት ዐቅም ያላትም ትመስለኛለች። …

 

የብርቱካን ሚደቅሳ “መመለስ” መጽሐፍ

መመለስ Memeles birtukan mideksa book buy

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በአቋም ጽናትና በአመራር ብቃቷ በምትታወቀው ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የተዘጋጀው “መመለስ፦ ቦጌ ትውስታዎቼ” የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል.

ብርቱካን ሚደቅሳ በዚህ መጽሐፏ ታሪኳን የተረከችበት፣ ልምዷን ያካፈለችበት፣አስገራሚውን የሕይወት ታሪኳን አጋርታናለች

The post መመለስ ቦጌ ትውስታዎቼ Memeles by Birtukan Mideksa first appeared on Addis Books.

]]>
https://addisbooks.com/book/memeles-birtukan-mideksa/feed/ 0