Yebirhan Felegoch - Addis Books

የብርሃን ፈለጎች Yebirhan Felegoch
የብርሃን ፈለጎች Yebirhan Felegoch book by Alemayehu Gelagay

ማጀቱን ቸል ብሎ የሰፈሩን መንገዶች ለማሰስ የደፈረ ሕጻን፣ ጎርምስና ሲያጣድፈው ጣፋጭና ጎምዛዛ ሕይወት እየዛቀ ሲበትን፣ ሳያውቀው የብይትውርናን በር ያንኳኳል፡፡ በብርሃን ፈለጎች ብርሃን የተነፈጉና ጭላንጭሉ ያጓጓቸው ገጸ ባህሪያት ተመልምለዋል፡፡ ጥቂት ናቸው፤ በለጋ እድሜያቸው የኑዛዜ ዕቃ ተረካቢ ይመስል የሕይወትን ጓዳ የሚበረብሩ፣ ዓለማየሁ ገላጋይ በግንብ ተከልለው ለሚነቅዙት ሳይሆን በየሜዳው ኳስና ኑሮን ለሚጠልዙት ነው ያደላው፡፡ በአጥቢያ፣ ቅበላና፣ ኩርቢት ኮስታራ ጭብጦችን የፈለቀቀው ደራሲ በየብርሃን ፈለጎች ለትልቅ ጉዳይ ሳይሆን ከውስጣዊ ጉዞ በመዝመት ልቦናን፣ ዕምነትን በቅኔያዊ ቋንቋ አወርዝቶ፣ ለፍቅር፣ ለድልና ሽንፈት ያቃስታል፡፡

ለፍቅር ሙዚቃን መቅሰም፣ ለወደዱት መብሰክሰክ፣ የመጀመሪያውን የወሲብ ሩካቤ አጣጥሞ ለሕይወት መበርገግ፣ የሙህር አዕምሮን ዘልቆ በማጤን እምነትን ለማርገብና ለማጥበቅ መታከት ግለሰብን ሲያደነድን የሚጤንበት ልቦለድ ነው፡፡ በአንድ ሁለት ምዕራፍ ከተረቅ ይልቅ ወደ ዘገባዊ ማውጠንጠን ልቦለዱ ሲዳዳው ቀርፈፍ ያለ ይምሰል እንጂ የሕይወት ምት ጥድፊያ ላይ ነው፡፡ በተለይ ሁለት የሚጋፉ ማንነቶች ነጠላ ግለሰብን ሲያዋክቡት፣ አንድ ራስን ማስገር ፈተና የሆነበት ልብወለድ ነው፡፡

የማኅበረሰብ፣ የቤተሰብ፣ የዘመድና ጎረቤት… በየጀምበሩ መፈነካከት፣ በየጓዳው ገመናን የመጋረድ ልክፍት ያስደምማል፡፡ የፍቅር ጥልቀት ሲሰውረን፣ ገና ለገና ከሌላዋ ተዳርቶ ይሆን የሚል ጭንቀት የሕላዌን ደስታ ለምን ያኮማሽሸዋል? ከቤትም ከጎዳናም ለኑሮ ጥሪና መዘዝ ልጅነትና ጉርምስናን አለዕድሜ መማገድ ለትውልድ እርግማን ነው በረከት?… ከአዕምሮአችን የሚንገዋለሉ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ ልቦለዱን አንብበን ስናበቃ እናውቀው የነበረ ሕይወት ጎምርቶ ጣዕሙን መለየት እስኪያቅተን የሆነ ሥጋት ይገጣጠባል፡፡ ዓለማየሁ ገላጋይን በቅርበት የሚያውቁት እስከ ዛሬ የደረሰው መለማመጃ እንጂ ገና ዋናውን ልሂቁን መች አስነበበን ይላሉ፡፡ ዶሮ ሳይሰፍር ወደ ምናብ መመለሱን ትቶ እስኪነጋ ይጓዝ ይሆን?

The post የብርሃን ፈለጎች Yebirhan Felegoch first appeared on Addis Books.