Cart

Addis Books

Addis Books

Yemata Injera book by Alemtsehay Wedajo
Yemata Injera book by Alemtsehay Wedajo

የማታ እንጀራ በዓለም ፀሐይ ወዳጆ Yemata Injera Alemtsehay Wedajo

የማታ እንጀራ በዓለም ፀሐይ ወዳጆ (Yemata Injera book by Alemtsehay Wedajo) አቅሜ ትዝብቶችን በስንኝ ቆጣጥሮ መዋል ማደር ነውና የማደንቀውንም የምወቅሰውንም ከትቤአለሁ፡፡ ተፈጥሮን . . . ውበትን ለመዳሰስ ሞክሬአለሁ፡፡ ዓርማዎቼን በሙገሣ ሳሽር የወገንን ችግርና ብሶት በመዳሰስ በተለይም በበቀሉበት በቅሎ ሳይመረት የሚሠፈረውንም ዘልፌአለሁ፡፡ ወድጄም አይደል! በሌላ በኩል እየሞቱ ለኖሩ አድናቆትን፣ እያሉ ለሞቱትም ትንሽ ዘራፍነትን ለመቸር ሞክሬአለሁ፡፡ የግጥም ዋይታዬ ወገንን በህብረት አጠንክሮ ተስፋን አጭሮ ለውጤት የሚረዳ ይሁንልኝ፡፡
$10.00
Yebirhan Felegoch Alemayehu Gelagay addisbooks
Hot

የብርሃን ፈለጎች Yebirhan Felegoch

ማጀቱን ቸል ብሎ የሰፈሩን መንገዶች ለማሰስ የደፈረ ሕጻን፣ ጎርምስና ሲያጣድፈው ጣፋጭና ጎምዛዛ ሕይወት እየዛቀ ሲበትን፣ ሳያውቀው የብይትውርናን በር ያንኳኳል፡፡ በብርሃን ፈለጎች ብርሃን የተነፈጉና ጭላንጭሉ ያጓጓቸው ገጸ ባህሪያት ተመልምለዋል፡፡ ጥቂት ናቸው፤ በለጋ እድሜያቸው የኑዛዜ ዕቃ ተረካቢ ይመስል የሕይወትን ጓዳ የሚበረብሩ፣ ዓለማየሁ ገላጋይ በግንብ ተከልለው ለሚነቅዙት ሳይሆን በየሜዳው ኳስና ኑሮን ለሚጠልዙት ነው ያደላው፡፡ በአጥቢያቅበላና፣ ኩርቢት ኮስታራ ጭብጦችን የፈለቀቀው ደራሲ በየብርሃን ፈለጎች ለትልቅ ጉዳይ ሳይሆን ከውስጣዊ ጉዞ በመዝመት ልቦናን፣ ዕምነትን በቅኔያዊ ቋንቋ አወርዝቶ፣ ለፍቅር፣ ለድልና ሽንፈት ያቃስታል፡፡
$9.99