Hot
በምሥራቅ በኩል By Solomon Sahele Tizazu
$15.00
በምሥራቅ በኩል Be Misrak Bekul a book By Solomon Sahele Tizazu.
Addis Books
Description
✒️ የብዕር ስንቅ
ሰለሞን ሳኅለ (ሶል) በግጥሞቹ ነፍሳችንን ሲያባባ፣ በአጫጭር ልቦለዶቹና በወጎቹ ደግሞ ስሜታችንን ሲገዛ ቆይቷል። አሁን ግን ረዥም፣ ዝርው እና እውነተኛ ታሪክን መሠረት ባደረገው “በምሥራቅ በኩል” በተሰኘ አዲስ ሥራው ብቅ ብሏል። ሶል ወደ አዲሱ የጽሕፈት ዘውግ ሲሻገር ማየት ለሁላችንም ትልቅ ጉጉት ነው።
📖 መጽሐፉ ምን ይዟል?
ይህ መጽሐፍ ዝም ብሎ ትረካ አይደለም፤ ይልቁንም፦
እውነተኛ ታሪክ፡ በመረጃና በሐቅ ላይ ተመርኩዞ የተቀመረ።
ጥልቅ ምርመራ፡ ከሐሳብ ደደር፣ ከስሜት ኮስተር ባለ መልኩ ታሪክንና ሰውን የመረመረ።
አዲስ ዘውግ፡ ሶል ከለመድነው የግጥም ዓለም ወጣ ብሎ በሰፊው የዝርው ጽሑፍ ጥበቡን ያሳየበት።
”ሰው ሲጎለምስ ታሪክን መመርመር፣ ማንነትን መፈለግ ግድ ይለዋል መሰል…”
ሶል በዚህ ሥራው የነገሮችን መጀመሪያና መድረሻ፣ የምሥራቁን ጮራና የተደበቁ እውነታዎችን በብዕሩ ቀርጾልናል። ጥንቅቅ ባለ ቋንቋና ማራኪ አገላለጽ የተሰናዳው ይህ መጽሐፍ፣ የደራሲውን ሁለገብነት የሚያሳይ ትልቅ ማሳያ ነው።
Reviews (0)
You must be logged in to post a review.






Reviews
There are no reviews yet.