Cart

No products in the cart.

Authors

Sirak Wondemu

Sirak Wondemu ማነው? ከታች ያለው የሲራክ መልእክት ነው! ሲራክ ወንድሙ እባላለሁ። የወራቤ ዩኒቨርስቲ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ የትምህርት ክፍል የኹለተኛ ዓመት ተማሪ ነኝ። ሥነ ጽሑፍ የሕይወቴ አንድ አካል በመሆኑ ስለምማረውም […]

Description

Sirak Wondemu ማነው? ከታች ያለው የሲራክ መልእክት ነው!

ሲራክ ወንድሙ እባላለሁ። የወራቤ ዩኒቨርስቲ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ የትምህርት ክፍል የኹለተኛ ዓመት ተማሪ ነኝ።

ሥነ ጽሑፍ የሕይወቴ አንድ አካል በመሆኑ ስለምማረውም ስለምሰራበትም እጅግ ደስተኛ ነኝ።በቋሚነት ባይሆንም ከ2014-2017 ድረስ ወጣ ገባ እያልኩ አዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ ፅፌያለሁ።

በ2016 ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተመጻሕፍት እና ቤተመዛግብት ኤጀንሲ(ወመዘክር) ጋር ሁለት የመጽሔት ሕትመቶች ላይ ተሳትፌያለሁ።

በዛው ዓመት በ2016 መጨረሻዎቹ አከባቢ አዘቦት የተሰኘ የአጭር አጭር የትረካ መጽሐፌን በ e-Book መጀመሪያ በአፍሮ ሪድ (ሀገር ውስጥ) በኋላም በ amazon Bookstore ላይ ማሳተም ችያለሁ።

በ2017 ክንፋም ከዋክብት የተሰኘ የ50 ገጣሚያን የግጥም መድብል ውስጥ እንደ አንድ ገጣሚ ተሳትፌያለሁ። ሌላም በዘሃ event አማካኝነት በጊዮን ሆቴል ይዘጋጅ በነበረው የሳቅ ተከሽኖ ወርሐዊ የጥበብ ምሽት ላይ በቋሚነት ለ1 ዓመት ያህል ሰርቻለሁ።

አሁን ላይም በባይራና መዲና ዲጂታል መጽሔቶች ላይ በመፃፍ እገኛለሁእንዲሁም የሥነ ጽሑፍ ሳሎን በተሰኘ የአንጋፋ ጸሐፊያን የውይይት መድረክ ላይ አባል ነኝ!!

Review

Customer Reviews

Write A Review