የደራሲ አበራ ለማ ግለ -ታሪክ መፅሐፍ ይመረቃል
“…እንዲህም ተኑሯል” የሚል ርዕስ ያለው በ550 ገፆች የተሰናዳው የደራሲና ጋዜጠኛ አበራ ለማ የሕይወት ታሪክ ምረቃ ቅዳሜ የካቲት 7 2018 ዓ.ም በወመዘክር ኅሩይ አዳራሽ ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።
በዕለቱ፣ ታላላቅ እንግዶች በተናጋሪነት የሚጋበዙ ሲሆን በግለ -ታሪክ መፅሀፉም ላይ የዳሰሳ ፅሑፍ ይቀርባል።
አበራ ለማ፣ ካገራችን ገጣሚያንና አጫጭር ልብ-ወለድ ጸሓፊዎች አንዱ ሲሆን በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነፅሑፍ ጥናት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂም፣ ነው።
አበራ፣ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ፕሬስ መምሪያዎች ሠርቷል። ከጦር ግንባር ጋዜጠኝነት እስከ ኪነ-ጥበባት ዘርፎች ሀያሲነት የዘለቀ ሲሆን በአንባቢያን ተወዳጅ የሆኑ ሥራዎችንም ለማስነበብ የቻለ ነው።
ከአበራ ለማ የታተሙ ሥራዎች የሚከተሉት ይጠቀሳሉ።
1967 ኩል ወይስ ጥላሸት፣ የግጥም መድብል፣
1974 ሽበት፣የግጥም መድብል፣
1975 ሕይወትና ሞት፣የአጫጭር ልቦለዶች መድብል፣
1976 ሞገደኛው ነውጤ፣ ኖቭሌት፣
1978 አባደፋር፣ከሌሎች ደራስያን ጋር… ስብስብ፣
1978 ጽጌረዳ ብእር፣ከሌሎች ገጣሚያን ጋር… ስብስብ፣ እና ሌሎችንም ከ21 በላይ መፅሐፍትን ፅፎ ለማስነበብ በቅቷል።
የዚህ መርሐ ግብር የክብር እንግዳ ዶክተር ኃይሉ አርአያ ሲሆኑ ከተናጋሪዎች መካከልም እመቤት ሆይ ፍሬአለም ሺባባው እና ኢንጂነር ቢጃይ ናይከር ይገኙበታል።