Cart

Authors

Tigist Wolde

ትዕግስት ወልዴ  የተወለደችው በሀረር ከተማ ልዩ ስሙ አደሬ ጢቆ በሚባል አካባቢ ሲሆን የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በቤተልሄም የካቶሊክ ትምህርት ቤት ተምራለች ። ከዛም ወደአዋሳ በማቅናት በደቡብ ዩንቨርስቲ ቢዝነስ ኤንድ ኢኮኖሚክስ

Author's Books

Deciding What to Read Next?

Description

ትዕግስት ወልዴ  የተወለደችው በሀረር ከተማ ልዩ ስሙ አደሬ ጢቆ በሚባል አካባቢ ሲሆን የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን በቤተልሄም የካቶሊክ ትምህርት ቤት ተምራለች ። ከዛም ወደአዋሳ በማቅናት በደቡብ ዩንቨርስቲ ቢዝነስ ኤንድ ኢኮኖሚክስ የመጀመሪያ ዲግሪዋን አግኝታለች ። ከምርቃት በኋላ የስራ ህይወቷን ሀ ብላ የጀመረችው በድሬዳዋ ከተማ ነው ። ለአንድ አመት ያህል በመንግስት መስሪያ ቤት ከሰራች በኋላ መስሪያ ቤቱን ለቃ የግል ስራ መስራት ጀምራለች።

ከልጅነቷ ጀምሮ ለስነፅሁፍ ባላት ፍቅር ምክንያት ከመፅሃፍት ተለይታ የማታውቀው ትዕግሥት አልፎ አልፎ መጫር የጀመረችው ከሃይስኩል ጀምሮ ነው ። የተወሰኑ አጫጭር ልቦለዶች በሃይስኩልና በዩንቨርስቲ ቆይታዋ ታዘጋጅ ነበር ።የመጀመሪያ የረጅም ልብወለድ ስራዋ የሆነውን “ያልነጋው ቀን” የተሰኘው መፅሃፏ በሚያዚያ ወር 2009 አ.ም ለህትመት በቅቷል ።

በቅርቡም አዲሱ መፅሀፏ “ገሊላ ” በዚህ አመት ታህሳስ 2018 ዓ.ም ለህትመት በቅቷል ።

Review

Customer Reviews

Write A Review

AddisBooks Ads