Cart

ገሊላ Gelila by Tigist Wolde 

ገሊላ Gelila a Book by Tigist Wolde.
Addis Books!
December 23, 2025 Amharic 202 pages

Authors

Meet the Author

Tigist Wolde

Book By Tigist Wolde View All
ገሊላ Gelila by Tigist Wolde 
ገሊላ Gelila by Tigist Wolde 

Description

ገሊላ Gelila by Tigist Wolde 

ገሊላ በወጣትነት እና ቁንጅና ላይ እርጋታን የተላበሰች የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ መምህርት ከዕለታት በአንዱ ቀን አንድ ድንገተኛ የስልክ ጥሪ ካልጠበቀችው ቦታ ይደርሳታል – ከአማኑኤል ሆስፒታል ። ደዋዩ በታታሪነትና በብሩህ አዕምሮው የምታውቀው አንድ ተማሪዋ ድንገተኛ የአዕምሮ ህመም እንደገጠመው እና በሆስፒታሉ የህክምና እርዳታ እየተደረገለት እንዳለ ፥ በአዕምሮ መታወክ ውስጥ ሆኖ ከሚጠራቸው ቦታዎችና ሰዎች ስም መካከል አንዷ እሷ መሆኗን ገልፆ ምንአልባት ልትጎበኘው ትችል እንደሆን ይጠይቃታል ።

ገሊላ ይህ ድንገተኛ የስልክ ጥሪ እና አሳዛኝ ክስተት ልቧን ነክቷት በአዕምሮ ህመም የሚሰቃየውን ተማሪዋን ለመጠየቅ በቅንነት መሄዷ ፈፅሞ ካልጠበቀችው ውስብስብ ታሪክና ለሷ ለራሷ እንኳ ፈፅሞ እንግዳ ከሆነባት ማንነቷ ጋር እንደሚያገናኛት ፈፅማ አልገመተችም ። ክስተቱ የፈጠረውን የተጠላለፈ የታሪክ ሰበዞች እንደ ፍንጭነት በመጠቀም ስትመረምር መላው ዓለም በጥብቅ የሚፈልገው የሰማያትን እና የምድርን ሚስጥራት የያዘ ፥ በሁሉም አጥናፍ ያሉ ፍጥረታትን እና ኃይላትን መቆጣጠር እና መግዛት የሚያስችል የንጉስ ሰለሞን የጥበብና የኃይል ምንጭ የሆነ ምስጢራዊና ምትኃታዊ መፅሀፍ ከሷ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለውና ይህን መፅሀፍ በሚስጥር ተደራጅቶ ከኢትዮጵያ ለመስረቅ እየታገለ ካለ ጠንካራ ቡድን ጋር ፊትለፊት ያጋፈጣት መሆኑን ትረዳለች …

* **
ገሊላ መፅሀፍ በመቼት ደረጃ ከእንግሊዝ እስከ አዲስ አበባ ፥ ከእንጦጦ ማርያም ቤተክርስትያን እስከ ወልድያ እና ግሸን ፥ ከደቡብ አፍሪካ እስከ ኮፐንሀገን ይሸፍናል ። በልብወለድ የዘውግ ምድብ (genre) ደረጃም የተወሳሰበ ምስጢርን መፍታት ላይ ያተኮረ ምስጢራዊ ልብወለድ (Mystrey Novel) ይመደባል ።

በዚህ በ 202 ገፆች የተሰናዳ ታሪክ ውስጥ ደራሲዋ ትዕግስት ወልዴ ውስብስብ የታሪክ አወቃቀር (Complex plot) መስራትን ችላበታለች ። በሳል የቋንቋ አጠቃቀም እና ገላጭ የሆነ ገፀባህሪ አሳሳል ችሎታዋም በጉልህ ይታያል ። እንደዚህ አይነት የማወቅ ጉጉትን የሚያጭር እና ሀገራዊ ጭብጥ ያላቸው መፅሀፍት በአብዛኛው አንባቢ ዘንድ እንደ በረከት የሚቆጠሩ በመሆናቸው የማንበብ ፍቅር ያለው አንባቢ ሁሉ ሊያነበው እንደሚገባ እጠቁማለሁ ።

[ፀኃፊ ሙላት ኪዳኔ ፥ በድሬዳዋ ዩንቨርስቲ የእንግሊዘኛ ስነፅሁፍ መምህር ]

* **

[ፀኃፊ ዮናዔል ]

በቅርቡ ገበያ ላይ የዋለውን “ገሊላ ” የሚለውን የትዕግስት ወልዴን የረጅም ልብወለድ መፅሃፍ ሳነበው ወደ አዕምሮዬ የመጣው የመጀመሪያው ጥያቄ ፦

‘ እዚህ መፅሃፍ ላይ የተፃፈው ታሪክ እውነት ነው እንዴ ?’
የሚል ነበር ያንን ያስጠየቀኝ የታሪኩ ልብ የመንካት ጉልበት ሳይሆን አይቀርም ።

አንድን ሀሳብ በውብ ገላጭ ቃላት ማቅረብ የትዕግስት ስጦታዋ ነው ብል ይቀለኛል ።የወንዱን ብዕር የለመድነው እኛ ኢትዮጵያውያን አንባቢዎች በሴት ብዕረኞች ውስጥ ያለው የአገላለፅ ብቃትን ልብ ብለን ማስተዋል እንዳለብን አሳስቦኛል ።ሴቶች በተፈጥሮዓቸው መዋብ እንደሚወዱ አውቃለሁ እንደሚጫሙት ጫማ ፥ እንደሚለብሱት ሸማ ቃላትንም መምረጣቸውንና መኳላቸውን ግን ይህን መፅሃፍ ሳነብ ነው ልብ ያልኩት ። ቃላቶቿ ውብ ናቸው ።ልብ አንጠልጣይ የሆነው ይህ ልብወለድ መፅሃፍ ሀገሩን የሚወድ ሁሉ ቆም ብሎና አሻግሮ ሊመለከታቸው የሚገቡ ውስብስብ ሴራዎችንም ይጠቁማል ።

Reviews

There are no reviews yet.

Be the first to review “ገሊላ Gelila by Tigist Wolde ”
AddisBooks Ads