Description
Demtse Kal ደምፀ ቃል: ስብስብ ግጥሞች by
“ደምፀ ቃል” – ቃላት ድምፅ ሲሆኑ
ቃላት ይነበባሉ ፣ ይሰማሉ
ቃል ስሜት ነው
ቃል ትዝታ ነው
ቃል ተስፋ ነው
ቃል ምስክርነት ነው
ቃል ማንነት ነው
ቃል ህይወት ነው
ቃል ድምፅ ነው።
“ደምፀ ቃል” የምልዕቲ ኪሮስ የግጥም መፅሀፍ፣ ቃልን ወደ ድምፅ፣ ስሜትን ወደ ግጥም፣ ግጥምን ወደ ትዝታ የሚያስጉዝ አዲስ የግጥም መድብል።
ምልዕቲ ኪሮስ በግጥም፣ በስክሪፕት ጽሑፍ፣ በዘፈን ግጥም እና በሬዲዮ ፕሮዳክሽን አቅራቢነት የተለያዩ ስራዎችን የሰራች ዘርፈ ብዙ የኪነ ጥበብ ባለሟል ።
ምልዕቲ የተለያዩ የዘፈን ግጥም ስራዎችን ለተለያዩ ታዋቂ ድምፃውያን ሰጥታለች ከነዚህም መካከል ለፍቅርአዲስ ነቃጥበብ፣ ለብስራት ሱራፌል፣ ለሄዋን ገ/ወልድ(ጃኖ) ፣ አህመድ ተሾመ ዲንቢ፣ ያሬድ ነጉ፣ ሜላት ቀለመወርቅ እና ለሌሎችም ድምፃውያን የሰጠች ሲሆን በሀገራችን የሙዚቃ ዘርፍም ላይ አሻራዋን እያኖረች ያለች ሁለገብ የኪነ ጥበብ ሰው ነች።
Reviews (0)
You must be logged in to post a review.














Reviews
There are no reviews yet.