Cart

Sefinaye ሠፊናዬ by Naod Wubetu

$20.00

Sefinaye ሠፊናዬ by Naod Wubetu.
Addis Books!
Amharic

Authors

Meet the Author

Naod Wubetu

Book By Naod Wubetu View All
Sefinaye ሠፊናዬ by Naod Wubetu
Sefinaye ሠፊናዬ by Naod Wubetu

Description

Sefinaye ሠፊናዬ by Naod Wubetu

ሠፊናዬ ግጥም ስብስብ መድብል በ 3 የመሸጋገርያ ፅሁፎች ተከፋፍላለች። የመጀመርያው ክፍል ‘አኗኗር..አኪያሄድ..ፍስሰት’ ላይ ያተኩራልለመፅሀፉ እንደ ዳዴታ ነው ሁለተኛው ደግሞ ‘ተብሰልስሎት እና የህይዎት ፍልስፍና ከኑሮ ውህደት ጋር’
የመጨረሻው ክፍል ‘ኢትኖግራፊ’አዊ ውበት ፣ ድመማ.. እና ከ 15 በላይ በሚሆን በሚሆኑ ሀገርኛ ቋንቋወች የተፃፈ የስብስብ ክፍል ነው።

ሠፊናዬ’ ማለት ‘መርከቤ’ እንደማለት ነው (ነፋስ የሚነዳት ባለ ሸራ መርከብ ነች)  ህይወትን የወከልኩባት መሸጋገርያ ነች። “ይዘት” ለሥነ-ግጥም በጉልህ አይከሰትልኝም ግን እንዴትም ቢሆን ማሰርያው ኑሮ እና አኗኗር(ህይወት) ነው።

አረንጓዴ አበባ

አረንጓዴ አበባ ህያው ህይወት መሳይ
ተስፋ፥ የሀሴት ሲሳይ

ቅጠልማ አበባ
የቅጠል ንቅሳት – እሳት የወረሳት

ወዲያ ወንዝ ዥረት ሀጫ በረዷማ፥ ተንሸራታች መሳይ
ወዲህ ዛፍ ስር እኔ፥ በዝምታ ዜማ በአደብ ሁሉንም ሳይ
መሀሉ የአበባ እርሻ
(ትዝታዋን መርሻ፥ ናፍቆቴን ማገርሻ . . .)
በጎን ግምብ አጥር የተከለከለ
ደሞ መከለያ () ደሞ መከልከያ ()
መሀሉ አበባማ ደምቆ ያሸበረቀ፥ ዕምቡጥ ዘላለማይ
ወንዝ ወዲህ ጨረቃ፥ ወንዝ ወዲያ ፀሀይ
ቀና ስል፦ ስዕል – ሰማዩ
አንፃር የለው ፍቅር፥ ፍትሕ የለው ፍርጃ
ወዲህ አበባ ነው፥ የወዲያውን እንጃ።

ዘላለም ይመስላል አሁን ይሄ ብቻ?
አሁን እኔ ብቻ!?
የተደገፍኩት ዛፍ ንፋስ ሽው ሲለኝ (ነፋሱ ሽውው ሲል)፥
በሰውነቴ ላይ አበባ ያረግፈል
አሁን ይሄም ያልፋል?

Reviews

There are no reviews yet.

Be the first to review “Sefinaye ሠፊናዬ by Naod Wubetu”
AddisBooks Ads