Description
Armageddon’s Gate የአርማጌዶን በር by
“..ደራሲነት በአንድ ጎልጎታ ሁለት መስቀል የመሸከም ዕዳ ነው፤ አንድም የራስ፤ አንድም የትውልድ ዕዳ።… ‘ባለ ቅኔ የሰው ልጅን ልቦና ሊያጠራ፣ ብሎም ሊያነቃ ግዴታ አለበት።’ እንደሚባለው ደራሲ ዓለማየሁ ደመቀ’ም የልቦናውን ሻማ ሲያቀልጥ የኖረው በዚህ መንገድ ነው። በሙዚቃ ሥራዎቹ ብዙ ልቦችን ለማከም ከሚተጋው እኩል በድርሰቶቹ በኩል የልቦናን ኩክ እያፀዳ ትውልድን ሲያነቃ ኖሯል። እነሆ ዛሬ ደግሞ ከዮቶር ቁጥር አንድ እና ቁጥር ሁለት የቀረውን ሚስጢር በ’አርማጌዶን በር’ በኩል ሊያወጋን ተከስቷል። ‘መዳንን የሚሻ ከጥበብ ይወዳጅ፤ በእምነትም ይፅና!’ ነውና ብሂሉ፤ ወደ ድግሱ ከተጠሩት የታደሉት ብቻ ጣፋጩን ወይን ይቀምሳሉ።…”
ተስፋዬ አየለ (ዶ/ር)
ከአርታዒው ማስታወሻ የተወሰደ
* * *
“..እርስ በእርሳችን ስንረጋገም ጠላታችንን እየመረቅነው ነው። አንተ የናቅኸውን ጥበብ ውድቀትህን የሚናፍቀው ይጠበብበታል። ቀድሞውንስ ታጣጥለው ዘንድ ማን ቀረጸህ? የአያቶችህ ጥበብ ፍሬ ፈርስኪ መስሎ እንዲታይህ የፈረንጅ ድግምት ተደግሞብሃል።…”
* * *
“… እነዚህ አጋንንት ከሰው ልጅ ነፍስ የሚመነጨውን የፍርሃትና የጥላቻ ረቂቅ ኃይል እየተመገቡ ስለሚኖሩ፣ እልፍ አዕላፍ ጦርነቶች ከምድር እንዳይጠፉ ተግተው ይሰራሉ።…”
ከመጽሐፉ የተወሰደ
Reviews (0)
You must be logged in to post a review.
AddisBooks Ads





Reviews
There are no reviews yet.