Description
“ትርኳሽ” (Tirkuash) በደራሲ ሰዒድ ሙህዬ አህመድ
“ትሰማኛለህ! እዚህ የተቀመጥነው አንተን ለማጫወት አይደለም፡፡ የምትናገር ከሆነ ቶሎ ተናገር ያለበለዚያ………” ብሎ ጠረጴዛውን በሃይል “ቷ!” ሲያደርገው ከተቀመጥኩበት አግዳሚ ወንበር ላይ ነጥሬ ተመለስኩ፡፡ በዚህ ሰዓት አውነትም ሀሰትም አኩል ሆኑብኝ። የአነሱን ፍላጎት ለማሟላት ያላደረግኩትን አድርጌያለሁ ብዬ ልናገርወይስ በውስጤ ያለውን አውነት ተናግሬ የተደገሰልኝን መከራ ልቀበል? በእርግጥ እውነቱን ተናግሬ በመሸበት ለማደር መጀመሪያ በህይወት መቆየት ይቀድማል፡፡ ለኔ በዚች የጭንቅ ሰዓት የሁለቱም መልሶቼ ምላሽ ተመሳሳይ ነው፡፡ ያንኑ ያረጀ ያፈጀ የቂም ሂሳብ ማወራረድ፡፡ አቃጥያለሁ ዘርፌያለሁ፤ብላቸውም ወንጀለኛ ብለው መውሰድ የፈለጉትን እርምጃ ሊወስዱ ተዘጋጅተዋል፡፡ አልዘረፍኩም፤ አላቃጠልኩም፤ ብዬ ብመልስላቸውም ወንጀሉን ስትፈጽም ከነማስረጃው እጅ ከፍንጅ ተይዘህ እንዲት ትክዳለህ ብለው የደገሱልኝን አርምጃ ከመውሰድ የሚያግዳቸው እንዳች ምድራዊ ሃይል እንደሌለ አውቀው ተዘጋጅተውበታል፡፡ የትኛውን እንደምናገር በጭንቀት ተወጥሬ ሳመነታ ከእስር ቤት ያመጣኝ ፖሊስ ጣልቃ ገባና…….
ከመፅሀፉ የተወሰደ
መጽሐፉን የት ማግኘት ይቻላል?
በጃፈር መጻሕፍት መደብር አና ሀሁ መጻህፍት መደብር
አድራሻ፦
ጃፈር መጻሕፍት መደብር
📍4Killo ብርሀን እና ሰላም ማተምያ ፊት ለፊት
📍መገናኛ መሰረት ደፋር ህንፃስር
📍Mexico ደብረወርቅ ህንፃ ንግድ ባንክ አጠገብ
📍ጀሞ ሚካኤል መብራቱ ጋር ሚናሞል ፊት ለፊት
📍4Killo አብርሆት ግቢ ውስጥ
📍ለገሀር ኖክ ማድያ አጠገብ
ቁ1,አራት ኪሎ አብርሆት ጎን
ሀሁ መጻህፍት መደብር
ቁ2,ሜክሲኮ ደብረወርቅ ታዎር ግራውንድ
ስልክ፦ 0911006705/0924408461
Reviews (0)
You must be logged in to post a review.
AddisBooks Ads



Reviews
There are no reviews yet.