Ye Dengay Anagariw Mastawesha የድንጋይ አናጋሪው ማስታወሻ by Daniel Kebede
$20.00
Ye Dengay Anagariw Mastawesha የድንጋይ አናጋሪው ማስታወሻ by Daniel Kebede.
Addis Books!
Description
Ye Dengay Anagariw Mastawesha የድንጋይ አናጋሪው ማስታወሻ by Daniel Kebede
ካገር እንደወጣን በፈረንጆቹ አባባል እንደሚጠራው ዳያሪ አዘውትሬ መፃፍ መጀመሬ የእዚህ መፅሀፍ ስር መሰረቱ ሊሆን ይችላል ብዬ እገምታለሁ።
በሗላም ከመፅሀፉ እንደምታነቡት አርት ለማጥናት ወደ ዩኒቨርስቲ ስገባ የምሰራው አርት አገሬንና የራሴን ማንነት የማስተዋወቂያ መድረክ አድርጌ ያዝኩት። ምክንያቱም ያኔ እኔና ቤተሰቤ ወደ አሜሪካን ከመጣንበት ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን የእዚህ አገር ህዝብ ስለ እኛ አገር እና ስለ ሕዝባችን ያላቸው አመለካከት በጣም እጅግ የወረደ ነው።
የአገራችን ሕዝብም ለዘመናት በረሀብ፣ በእርስ በእርስ ጦርነት፣ በመፈናቀል እንደታመሰ ሁሌ ስለሚታወቅ አብዛኛውን ግዜ ስለ አገራችን ከተወራ ስለ እኛ ድህነት መታረዝ እና መጎሳቆል ብቻ ነው ወሬው። ሰለጠኑ የሚባሉት አገሮች እኛን የሚያውቀን መናጢ ድሆች ሁሌ በጦርነት የምንታመስ የምንበላው እንኳን የሌለን እዚህ መጥተን ሁሉን ነገር ለመጀመሪያ ግዜ ያየን አድርገውን ነው የሚቆጥሩን። እንኳን መኪናና ትላልቅ ህንፃ ማየት ይቅርና ዝናብ እንኳን ለመጀመሪያ ግዜ አሜሪካ ስገባ ያየሁ የመሰላቸውም አጋጥሞኝል።
ታዲያ እንዲህ ባለ ሁኔታ ቅስሙና ሞራሉ ተከስክሶና ተፈጭቶ ላለ ሰው ብናኙን ወኔ ይዞ መነሳት አማራጭ የሌለው ግዴታው ነው ብዬ አስባለሁ።
ስለእዚህ አጋጣሚ ባገኘሁ ቁጥር አገሬን ለማያውቁ ስለ አገሬ የምተርክበት መንገድ እፈልግ ገባሁ። ቅርፅ ከሰራሁ፣ አጭር ትረካ ካለኝ፣ ያገሬን ምግብ ሰርቼ ካበላሗቸው፣ ብና ቆልቼ ካጠጣሗቸው፣ ሁሌ አገሬ የት እንደነበረች የማውራበት መድረክ በመሻት ነው።
Reviews (0)
You must be logged in to post a review.



Reviews
There are no reviews yet.