Description
by Alemayehu Mammo
ማዕበል የውኃ መናወጥ ነው። ነውጡ በሐይቅ ፤ባሕር ወይም ውቅያኖስ ላይ ተደጋግሞ ይታያል። እንደ ቀድሞ መርከበኛ ማዕበልን ከነግርማው አውቀዋለሁ። እሹሩሩ ከሚለው ለስላሳ የውኃ ንቅናቄ ጀምሮ በታላቅ ድንፋታ እስከሚገፋተረው ወጀብ ድረስ እስኪበቃኝ ቀምሼዋለሁ። የዚህች መጽሐፍ ዓላማ ግን ውኃው በመርከቦችና በውስጡም ባሉ ሰዎች ላይ የሚያደርሰውን እንግልት መተረክ አይደለም። ይልቁንም እንደ ማዕበል ስለሚያንገላታን ምድራዊ ኑሮ ግንዛቤን ማስጨበጥ ነው። ከምንም ይልቅ የዚህች ጥራዝ ተልዕኮ የማዕበል መንገደኞች መሆናችንን ማስታወስ ነው።ስለሆነም በማዕበል የተመሰሉትን ስደትና መከራን ሌሎቹንም ተመሳሳይ አሳቦች በተነጻጻሪ ለመተንተን ሞክሬያለሁ። ተዛማጁን እውነታም ከባሕርያቸው ጋር አዳምሬ ዳስሻለሁ። ማዕበሉ የሚያመጣውን ንጦሽ ብቻ ተርኬ አላቆምኩም። ይህም አለ እንዴ ካላሰኘ በቀር ጥቅማጥቅሙንም በጥቂቱ ጨለፍ አድርጌያለሁ። በመጨረሻም ማዕበሉ መምጣቱ ሞገዱም መነሣቱ ካልቀረ አልፈነው ለመሄድ እሚረዱንን ጥቂት ነጥቦች አንስቻለሁ።
Reviews (0)
You must be logged in to post a review.
AddisBooks Ads



Reviews
There are no reviews yet.