Cart

No products in the cart.

Alemayehu Gelagay

ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ሕይወትና ክህሎት Alemayehu Gelagay
Alemayehu Gelagay
Hot

ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ሕይወትና ክህሎት

ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ሕይወትና ክህሎት በዓለማየሁ ገላጋይ The life of Sebhat Gebre-Egziabher and his skills book by Alemayehu Gelagay   የዓለማየሁ ገላጋይ ሥራዎች: "ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ሕይወትና ክህሎት"፣ "ቅበላ"፣ "የብርሃን ፈለጎች"፣ "ኢህአዴግን እከሳለሁ"፣ "ኩርቢት"፣ "ወሪሳ"፣ "አጥቢያ"፣ "የፍልስፍና አፅናፍ"፣ "በፍቅር ስም"፣ "መለያየት ሞት ነው"፣ "በእውነት ስም (ታለ)"፣ "ውልብታ"፣ "በእምነት ሥም(ሐሰተኛው)"፣ "የተጠላው እንዳልተጠላ" "ቤባኒያ (ዕውነት ሐሰት)"፣ "ማዕበል ጠሪ ወፍ"፣ የተሰኙ ልቦለድና ኢልቦለድ መፃሕፍት ለአንባቢያን አበርክቷል። ከዚህ በተጨማሪም "መልክዓ–ስብሐት" በተሰኘው መጽሐፍ 27 ጸሐፊያን፣ ደራሲያን፣ ገጣሚያንና ሰዓሊያን አሳትፎ በማሰናዳት ለአንባብያን አድርሷል።
$5.99
werisa alemayehu gelagay addisbooks
Alemayehu Gelagay
Hot

ወሪሳ (የውድቀት ፈለጎች) Werisa (Yewidket Felegoch)

Werisa (Yewidket Felegoch) (Paper Cover) ወሪሳ (የውድቀት ፈለጎች) By Alemayehu Gelagay አንድ የአማርኛ መምህር ከአርሲ ነገሌ በሰራ ቅያሪ አዲስ አበባ ወደምትገኝ ወሪሳ በምትባል ሰፈር አክስቱ ለጊዜው ወዳወረሱት ቤት ይገባል:: መምህሩ በዚህች ሰፈር እንዲሁም በጎረቤት ሰፈሯ "እሪ በከንቱ" የሚያጋጥመውን የመላመድና የመኖር ፈተና ፣ ግጭት ፣ መስማማት ፣ ተንኮል ፣ ፍቅር ፣ አጣብቂኝ ፣ ውዝግብ ፣ እንዲሁም የሚሰማቸውን ወግና ታሪክ(ተረት) ይተርካል:: መፅሐፉ የሚያነሳችው ወጎች ፣ ተረትና ምሳሌዎች ፣ ታሪኮች(ተረቶች) ተምሳሌያዊነትን ያዘሉ ሲሆን የኢትዮጵያን ያለፈ እና የአሁኑን ታሪክ: የአሁኑ ትውልድ የሚያይበትን የተዛባ ዓይን ፣ በአሁኑ ትውልድ ውስጥ ስላሉት የተለያዩ ነባራዊ ሐቆች እንዲሁም ልዩነት ያላቸው ተጎራባቾች ላለፈው ታሪክ የሚያድርጉትን ሽሚያ እና ሽኩቻን ያሳያል::
$5.99
Yebirhan Felegoch Alemayehu Gelagay addisbooks
Hot

የብርሃን ፈለጎች Yebirhan Felegoch

ማጀቱን ቸል ብሎ የሰፈሩን መንገዶች ለማሰስ የደፈረ ሕጻን፣ ጎርምስና ሲያጣድፈው ጣፋጭና ጎምዛዛ ሕይወት እየዛቀ ሲበትን፣ ሳያውቀው የብይትውርናን በር ያንኳኳል፡፡ በብርሃን ፈለጎች ብርሃን የተነፈጉና ጭላንጭሉ ያጓጓቸው ገጸ ባህሪያት ተመልምለዋል፡፡ ጥቂት ናቸው፤ በለጋ እድሜያቸው የኑዛዜ ዕቃ ተረካቢ ይመስል የሕይወትን ጓዳ የሚበረብሩ፣ ዓለማየሁ ገላጋይ በግንብ ተከልለው ለሚነቅዙት ሳይሆን በየሜዳው ኳስና ኑሮን ለሚጠልዙት ነው ያደላው፡፡ በአጥቢያቅበላና፣ ኩርቢት ኮስታራ ጭብጦችን የፈለቀቀው ደራሲ በየብርሃን ፈለጎች ለትልቅ ጉዳይ ሳይሆን ከውስጣዊ ጉዞ በመዝመት ልቦናን፣ ዕምነትን በቅኔያዊ ቋንቋ አወርዝቶ፣ ለፍቅር፣ ለድልና ሽንፈት ያቃስታል፡፡
$9.99