Loading Events
የአርቲስት ሥዩም ተፈራ የ77ኛ ዓመት ልደት እና የ5ኛው መጽሐፍ ምረቃ
የታላቁ የኪነ-ጥበብ ሰው አርቲስት ሥዩም ተፈራ የ77ኛ ዓመት ልደት እና 5ኛ መጽሐፍ ምረቃ መርሃ ግብር ይካሄዳል
በኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ታሪክ ውስጥ ጉልህ አሻራ ያሳረፉት ታዋቂው አርቲስት ሥዩም ተፈሪ የ77ኛ ዓመት የልደት በዓላቸውን እና የአምስተኛ መጽሐፋቸውን ምረቃ በጋራ የሚያከብሩበት ልዩ የኪነ-ጥበብ መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል።
በዕለቱ በርካታ ታዋቂ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ ደራሲያን፣ ጋዜጠኞች እና የጥበብ ወዳጆች የሚታደሙ ሲሆን፥ የተለያዩ ስነ-ፅሁፋዊ እና ጥበባዊ ዝግጅቶች ለታዳሚው ይቀርባሉ።
ቀን፡ ጥቅምት 28, 2019 ዓ.ም

ሰዓት፡ ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ

ቦታ፡ ጎሮ አደባባይ ሰማራ ሆቴል (ወደ ቱሉ ዲምቱ መንገድ 50 ሜትር ዝቅ ብሎ )
ለበለጠ መረጃ እና ለትኬት ማሳሰቢያ በስልክ ቁጥር 0911125788 መደወል ይቻላል።

Leave a Reply