Loading Events
  • This event has passed.

ለመቆያ አድማጮች በሙሉ እነሆ ታላቅ የምሥራች! 

ለዓመታት በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 የራዲዮ ማዕበል ልዩ ለዛ ባለው ድምፃቸው፣ ስሜት በሚነኩ ታሪኮችና የሕይወት ፍልስፍናዎች አእምሯችንን ሲያነጹና ልባችንን ሲያሞቁ የኖሩት ተወዳጁ ጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ (እሸቴ ከጃንሜዳ)፤ ያንን ድንቅ “መቆያ” የተሰኘ ዝግጅታቸውን አሁን “እነሆ መቆያ” (ቅጽ 1) በሚል ድንቅ መጽሐፍ ይዘውልን ቀርበዋል።
የደራሲውን ፊርማ እያገኘን መጽሐፉን በደስታ የምንረከብበት ልዩ የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ተዘጋጅቷል፤
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!
 ቀን፦ ቅዳሜ መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም
 ሰዓት፦ ከቀኑ 8:00 – 10:00
 ቦታ፦ አዲሱ የጃዕፈር መጻሕፍት መደብር 

ለበለጠ መረጃ፦ 0911 125324

Location

Location
Jaffar Books
Address
https://maps.app.goo.gl/KW36ctGcWbGkpvzH8
Addis Ababa, Ethiopia

Leave a Reply