ነገረ መጻሕፍት፦ “የጥበብ ቃሊም ሥነ-አዳም” አዲስ መጽሐፍ ውይይት ላይ በነፃ ተጋብዘዋል!
የሥነ-ጽሑፍ አፍቃሪያን በሙሉ፤ የፊታችን ቅዳሜ ልዩ የሥነ-ጽሑፍ ዝግጅት ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል። በትዕግሥት ሳሙኤል እና በቢኒያም አቡራ (አቡሬ) በጋራ የተሰናዳው “የጥበብ ቃሊም ሥነ-አዳም” የተሰኘው አዲስ መጽሐፍ ይመረቃል።
ዕለት: ቅዳሜ ጥቅምት 14/2019 ዓ.ም
ሰዓት: ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ: በፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ (Forum for Social Studies – FSS) ሕንፃ
አድራሻ: ቀበና ካቶሊክ ኪዳነምሕረት ቤተክርስቲያን አቅራቢያ፤ ወደ ሳንድፎርድ ትምህርት ቤት በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው አዲሱ ሕንፃ
📞 ለበለጠ መረጃ : 0976066720/0900651010
ኑ አብረን ጥበብን እንቋደስ ፍቅራችሁና መገኘታችሁ ለደራሲያኑ ትልቅ ብርታት ነው።