የደራሲ ገስጥ ተጫኔ አዲስ መጽሐፍ የፊርማ ሥነ-ሥርዓት!
ለመላው የመጽሐፍ አፍቃሪያን፣ አንባቢያን እና የጥበብ ወዳጆች በሙሉ “ነበር 1” እና “ነበር 2” በሚሉት ተወዳጅ መጻሕፍቱ የሚታወቀው አንጋፋው ደራሲ ገስጥ ተጫኔ አዲስ ያበረከተው “የእስረኛው ማስታወሻ” የተሰኘው መጽሐፍ የምረቃና የፊርማ ሥነ-ሥርዓት በታላቅ ድምቀት ይከናወናል። በእለቱ ተገኝታችሁ ከመጽሐፉ ደራሲ ጋር እንድትገናኙና የፊርማቸውን መጽሐፍ እንድትሸምቱ በታላቅ አክብሮት ተጋብዛችኋል።
ቀን: ቅዳሜ ጥቅምት 21 2019 ዓ.ም
ሰዓት: ከቀኑ 8:00 እስከ 10:00
ቦታ: አዲሱ የጃዕፈር መጻሕፍት መደብር ለገሃር፣ ተወልደ ሕንጻ
ስልክ ቁጥር: 0911 125324
ቅዳሜን በንባብና በዕውቀት አብረን እናሳልፍ!