-
የመጽሐፍ ምረቃ የክብር ጥሪ! የከበራችሁ የጥበብና የታሪክ ወዳጆች፤ በመምሕርና ጋዜጠኛ ተስፋዬ መኩሪያ ሉጋ ከዚህ ቀደም ከሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር ሆነው "ጎጎት" የተሰኘ መጽሐፍ ለአንባቢያን ማቅረባቸው ይታወቃል። አሁን ደግሞ የማህበረሰባችንን ባህላዊ የዳኝነት ስርዓቶች፣ የትውልድን የህይወት ውጣ ውረድ፣ የሶስቱን የመንግስት ስርዓታት ገጠመኞች እና የህዝቦችን ታሪካዊ ትስስር አቆራኝቶ የያዘውን "አቅል ግዛ" የተሰኘ አዲስ የታሪክ ቀመስ ልቦለድ መጽሐፍ ይዘውልን ቀርበዋል!