Cart

Fiction

Altezewawerechim
Hot

አልተዘዋወረችም Altezewawerechim

  ፍቅር ሁሉ ፍቅር አይደለም። በደፈናው አፈቀርን ወይም ተፈቀርን እንበል እንጅ ሰዎች ምናችንን በምን ምክንያት እንደወደዱልን በእርግጠኝነት መናገር የሚቻል ነገር አይደለም። ሰዎች ከማንነት በላይ ለአካላዊ ውበት በፍቅር ሊወድቁ ይችላሉ፤ ምናልባትም ይህ ለራሳቸውም አይገባቸውም ይሆናል። ከነጭራሹ «ወደድናችሁ» ያሉን ሰዎች እንደወደዱን ማረጋገጫችንስ ምንድነው ? ትዳር ? ስጦታ? ቃልኪዳን? ለእኛ የሚከፍሉት መስዋዕትነት? በመኖር ብቻ የሚመለስ ጥያቄ ሳይሆን አይቀርም። በዚህ መፅሐፍ ከነመኖራቸው ትዝ የማይሉን ጥቃቅን ስሜቶች ስንጥቃቸው እየሰፋ ሕይዎትን ለከባድ ምስቅልቅል ሲዳርጉ እናያለን። «ምናለበት» ተብለው ችላ የተባሉ እንደውም እንደበጎ ነገር የሚታዩ ጉዳዮች በጥልቀት ሲቃኙ ያላቸውን አደገኛ ስር እንመለከታለን። በሕይዎት ውስጥ « ቁጭ ብለን የሰቀልነውን ቁመን ማውረድ ሲያቅተን» ሌሎች ድሎት ያሉት ነገር ለሌላው መከራ ሲሆኑ ፣ እንታዘባለን። ፅናት፣ ፍቅር ፣ ስደት ፣ናፍቆት ፣ዓላማ ፣ ሐዘን ፣ደስታ ፣ በውብ ትረካ ተሰድረው እናገኛቸዋለን። እንደቀላል የልጅነት ሁዳዳችን ላይ የተጣለች ቅንጣት የቃል ዘር በኋለኛው ዘመናችን ዛፍ ሁና ጥላዋን በአኗኗራችን ላይ ስታጠላ እንታዘባለን። በመጨረሻም መፅሐፉን ስንከድን የራሳችንን ሕይወት ከፍተን መመልከት እንጀምራለን። 
$5.99
እመጓ: Emegua (Afrikaans Edition)

እመጓ: Emegua by Dr.Alemayehu Wassie

ከመጽሃፉ የተወሰደ "በቅዱሱ ዋሻ ውስጥ ምን እንደደረሰብኝ ቁልጭ ብሎ ታወሰኝ። ከጨለማው ክፍል በፍጥነት ወጥቼ በወርቃማ ጥልፍ ሥዕል ያማረውን ሐምራዊ መጋረጃ ጫፉን በእጄ አጥብቄ ይዤ ከታች ወደ ላይ ከቀኝ ወደ ግራ በፍጥነት ገለጥ ሳደርገው ድንገት ምንነቱን ያላወቅሁት የብርሃን ጎርፍ ከአስደንጋጭ መብረቃዊ ኃይል ጋር ተጣምሮ ወደ ላይ አንሥቶ ማዶ ካለው የዋሻ ቋጥኝ ጋር አላተመኝ። ድንጋጤና ከባድ ሕመም ተዳምረው ወዲያው ራሴን አሳቱኝ። ከዚያ በኋላ የሆነውን የማስታውሰው ነገር አይደለም። በመጨረሻ አሁን በእማሆይ ዕሴተ ማርያም አስታማሚነት ራሴን ሞላሌ ጤና ጣቢያ አገኘሁት። “አለመሞቴ ተመስገን ነው!” አልኩና እንባዬን መጠራረግ ጀመርሁ። " Publisher ‏ : ‎ EnjeraPress Publication date ‏ : ‎ September 7, 2025 Language ‏ : ‎ Afrikaans Print length ‏ : ‎ 206 pages ISBN-10 ‏ : ‎ 1969702001 ISBN-13 ‏ : ‎ 978-1969702006 Item Weight ‏ : ‎ 13.1 ounces Dimensions ‏ : ‎ 6 x 0.47 x 9 inches Best Sellers Rank: #885,547 in Books (See Top 100 in Books) #9,670 in Action & Adventure Fantasy (Books) #15,074 in Classic Literature & Fiction #18,390 in Memoirs (Books)
$29.99
keletat gimash qen
ከዕለታት ግማሽ ቀን KE ELETAT GIMASH QEN Alex Abraham

ከዕለታት ግማሽ ቀን KE ELETAT GIMASH QEN

Alex Abraham is one of the most influential young voices in modern Amharic literature. His bestselling books have earned wide acclaim for their powerful exploration of love, injustice, and social change, blending Ethiopian tradition with contemporary storytelling. "ከዕለታት ግማሽ ቀን" /Ke eletate Gmash Ken/his fifth book, continues this journey—offering a sharp, compelling look at the human experience and the challenges shaping society today.
$15.00
werisa alemayehu gelagay addisbooks
Alemayehu Gelagay
Hot

ወሪሳ (የውድቀት ፈለጎች) Werisa (Yewidket Felegoch)

Werisa (Yewidket Felegoch) (Paper Cover) ወሪሳ (የውድቀት ፈለጎች) By Alemayehu Gelagay አንድ የአማርኛ መምህር ከአርሲ ነገሌ በሰራ ቅያሪ አዲስ አበባ ወደምትገኝ ወሪሳ በምትባል ሰፈር አክስቱ ለጊዜው ወዳወረሱት ቤት ይገባል:: መምህሩ በዚህች ሰፈር እንዲሁም በጎረቤት ሰፈሯ "እሪ በከንቱ" የሚያጋጥመውን የመላመድና የመኖር ፈተና ፣ ግጭት ፣ መስማማት ፣ ተንኮል ፣ ፍቅር ፣ አጣብቂኝ ፣ ውዝግብ ፣ እንዲሁም የሚሰማቸውን ወግና ታሪክ(ተረት) ይተርካል:: መፅሐፉ የሚያነሳችው ወጎች ፣ ተረትና ምሳሌዎች ፣ ታሪኮች(ተረቶች) ተምሳሌያዊነትን ያዘሉ ሲሆን የኢትዮጵያን ያለፈ እና የአሁኑን ታሪክ: የአሁኑ ትውልድ የሚያይበትን የተዛባ ዓይን ፣ በአሁኑ ትውልድ ውስጥ ስላሉት የተለያዩ ነባራዊ ሐቆች እንዲሁም ልዩነት ያላቸው ተጎራባቾች ላለፈው ታሪክ የሚያድርጉትን ሽሚያ እና ሽኩቻን ያሳያል::
$5.99