Cart

No products in the cart.

Fiction

Altezewawerechim
Hot

አልተዘዋወረችም Altezewawerechim

  ፍቅር ሁሉ ፍቅር አይደለም። በደፈናው አፈቀርን ወይም ተፈቀርን እንበል እንጅ ሰዎች ምናችንን በምን ምክንያት እንደወደዱልን በእርግጠኝነት መናገር የሚቻል ነገር አይደለም። ሰዎች ከማንነት በላይ ለአካላዊ ውበት በፍቅር ሊወድቁ ይችላሉ፤ ምናልባትም ይህ ለራሳቸውም አይገባቸውም ይሆናል። ከነጭራሹ «ወደድናችሁ» ያሉን ሰዎች እንደወደዱን ማረጋገጫችንስ ምንድነው ? ትዳር ? ስጦታ? ቃልኪዳን? ለእኛ የሚከፍሉት መስዋዕትነት? በመኖር ብቻ የሚመለስ ጥያቄ ሳይሆን አይቀርም። በዚህ መፅሐፍ ከነመኖራቸው ትዝ የማይሉን ጥቃቅን ስሜቶች ስንጥቃቸው እየሰፋ ሕይዎትን ለከባድ ምስቅልቅል ሲዳርጉ እናያለን። «ምናለበት» ተብለው ችላ የተባሉ እንደውም እንደበጎ ነገር የሚታዩ ጉዳዮች በጥልቀት ሲቃኙ ያላቸውን አደገኛ ስር እንመለከታለን። በሕይዎት ውስጥ « ቁጭ ብለን የሰቀልነውን ቁመን ማውረድ ሲያቅተን» ሌሎች ድሎት ያሉት ነገር ለሌላው መከራ ሲሆኑ ፣ እንታዘባለን። ፅናት፣ ፍቅር ፣ ስደት ፣ናፍቆት ፣ዓላማ ፣ ሐዘን ፣ደስታ ፣ በውብ ትረካ ተሰድረው እናገኛቸዋለን። እንደቀላል የልጅነት ሁዳዳችን ላይ የተጣለች ቅንጣት የቃል ዘር በኋለኛው ዘመናችን ዛፍ ሁና ጥላዋን በአኗኗራችን ላይ ስታጠላ እንታዘባለን። በመጨረሻም መፅሐፉን ስንከድን የራሳችንን ሕይወት ከፍተን መመልከት እንጀምራለን። 
$5.99
Yebirhan Felegoch Alemayehu Gelagay addisbooks
Hot

የብርሃን ፈለጎች Yebirhan Felegoch

ማጀቱን ቸል ብሎ የሰፈሩን መንገዶች ለማሰስ የደፈረ ሕጻን፣ ጎርምስና ሲያጣድፈው ጣፋጭና ጎምዛዛ ሕይወት እየዛቀ ሲበትን፣ ሳያውቀው የብይትውርናን በር ያንኳኳል፡፡ በብርሃን ፈለጎች ብርሃን የተነፈጉና ጭላንጭሉ ያጓጓቸው ገጸ ባህሪያት ተመልምለዋል፡፡ ጥቂት ናቸው፤ በለጋ እድሜያቸው የኑዛዜ ዕቃ ተረካቢ ይመስል የሕይወትን ጓዳ የሚበረብሩ፣ ዓለማየሁ ገላጋይ በግንብ ተከልለው ለሚነቅዙት ሳይሆን በየሜዳው ኳስና ኑሮን ለሚጠልዙት ነው ያደላው፡፡ በአጥቢያቅበላና፣ ኩርቢት ኮስታራ ጭብጦችን የፈለቀቀው ደራሲ በየብርሃን ፈለጎች ለትልቅ ጉዳይ ሳይሆን ከውስጣዊ ጉዞ በመዝመት ልቦናን፣ ዕምነትን በቅኔያዊ ቋንቋ አወርዝቶ፣ ለፍቅር፣ ለድልና ሽንፈት ያቃስታል፡፡
$9.99