ዝንቡላ እና ካሮት Zinbula and Carrot by Tagel Seifu , Makida Arshi
ዝንቡላ እና ካሮት Zinbula and Carrot by Tagel Seifu , Makida Arshi
Addis Books!
ከአመጿ ጀርባ Ke Ametsua Jerba by Eden Habtamu
ከአመጿ ጀርባ Ke Ametsua Jerba, a book by Eden Habtamu.
Addis Books!
ሃያ ሶስት 23 by Daniel Abreha
ሃያ ሶስት "23" Haya Sost, a book by Daniel Abreha.
ሃያ ሶስት "23" በሊቢያ በረሃ በአይሲስ (ISIS) እጅ ወድቆ በሕይወት የተረፈው የዳንኤል አብርሃ እውነተኛ የጉዞ ታሪክ ነው። የመጽሐፉ ርዕስ "23" የተባለው ዳንኤል አብሮአቸው ከነበሩትና በአይሲስ ታግተው ከነበሩት 23 ኢትዮጵያውያን መካከል አንዱ በመሆኑ ነው።
Addis Books!
$25.00
መመለስ ቦጌ ትውስታዎቼ Memeles by Birtukan Mideksa
Memeles A book by Birtukan Midekssa. Boge Tewestawoche - መመለስ ቦጌ ትውስታዎቼ
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በአቋም ጽናትና በአመራር ብቃቷ በምትታወቀው ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የተዘጋጀው "መመለስ፦ ቦጌ ትውስታዎቼ" የተሰኘ ርዕስ የተሰጠው አዲስ መጽሐፍ ለንባብ በቅቷል። ብርቱካን ሚደቅሳ በዚህ መጽሐፏ ታሪኳን የተረከችበት፣ ልምዷን ያካፈለችበት፣አስገራሚውን የሕይወት ታሪኳን አጋርታናለች።
Memeles book by Birtukan Midekssa
888
This book contains the gematria of the Geez alphabet. There are 26 letters of Geez and each letter has a number that it represents and can reach up to 800. This 888 book uncovers the spiritual and scientific codes hidden in the Geez alphabet through Geez gematria. The author of the book is Dr Rodas Tadese Abebe and he has published 25 research books.
አንባብያን 888 የሚለውን ርእሱን በሚያዩበት ጊዜ ምን
ይኾን? ለምን ይኽነን ርእስ መረጠው? ሳይሉ እንደማይቀሩ እገምታለኍ፡፡ ይኸውም ከ6 ዓመታት በፊት ላይ "ቀመር 888 እና መጽሐፍ ቅዱስ" በሚል ርእስ "888" ከወሩ፣ ከቀኑ፣ ከዓመቱ ጋር
መገጣጠሙን በማሰብ በ2008 ዓ.ም. በቀን 8 በ8ተኛ ወር ላይ በፌስቡክ ላይ ዘርዘር አድርጌ በመጻፍ ለአንባብያን አንድ ጽሑፍ አጋራኊ፡፡ ያነንም ጽሑፍ ብዙዎች በጊዜው አንብበውት ነበር፡፡
የሚገርመው ነገር ከ6 ዓመታት በኋላ በ2014 ዓ.ም. ልክ ያነን ጽሑፍ በለቀኩበት ዕለት በ8ኛው ወር በሚያዝያ፣ በ8ተኛው ቀን፣ በ8ኛው ሰዓት ላይ 24ተኛው መጽሐፌ "ማዛሮት" በድምቀት ተመረቀ፡፡ በዚያ የመጽሐፍ ምረቃት መርሐ ግብር ላይ ኾኜ ይኽነን ግጥጥሞሽ ችላ ብዬ አልተመለከትኩትም፡፡
ይልቁኑ እንደ ትልቅ ምልክት በማሰብ በዚያው መጽሐፌ በሚመረቅበት ዕለት ይኽነን የ888 ምስጢርን፣ ይልቁኑ በግእዝ ፊደላት ውስጥ ያሉትን አቅማራትን፣ ምድራዊና ሰማያዊ ምስጢር ለአንባብያን አዘጋጅቼ ለማቅረብ ለራሴ ቃል ገባኊ፡፡
የወርቅ ዘንግ መጽሐፍን ለአንባብያን ያበቃው በቀመር 7 ላይ ምርምር የሚያደርገው መምህር መስፍን ሰሎሞንም ይኽነን
ዕውቀት በልቤ ይዤው እንዳልቀር ይልቁኑ ለትውልድ በጽሑፍ እንዳስተላልፈው አብዝቶ ይጠይቀኝ ስለነበር እንድጽፈው አንዱ ምክንያት ስለኾነኝ በዚኹ አጋጣሚ አመሰግናለኊ፡፡
የትምህርት ታላቁ ግብ አስቀድሞ ራስን ማወቅ ከዚያም በዕውቀት፣ በጥበብ ብርሃንነት ሐሰትን ከእውነት፣ ብርሃንን ከጨለማ መለየት፣ ሀገርን በቅንነት፣ በእውነተኛነት ማገልገል እንጂ በአንድ የማሠልጠኛ ተቋም ውስጥ ገብቶ የመመረቂያ ልብስ
ለብሶ፣ የምስክር ወረቀት መቀበል ብቻ አይደለም፡፡
በመኾኑም የኹላችኹም የኢትዮጵያውያን ሀብት የኾነው
ይኽነን ፊደል ለብዙ ሺሕ ዘመን የያዘውን ታላቅ ጥበብና ሰማያዊ ምስጢርን በዕውቀት፣ በማስተዋል መረዳት ስትዠምሩ ያን ጊዜ ፊደላችኹን መውደድ፣ ማክበር፣ መጠበቅ ትዠምራላችኊ፡፡
በዚኹ አጋጣሚ ፊደላችን የያዘውን ታላቅ ምስጢር ዐውቀው በምቀኝነት ለማጥፋት ከሚተጉ ከክፋት ሰራዊት፤ ዳግመኛም አለማወቅ ድቅድቅ ጨለማ ነውና ሳያውቁትም
በሞኝነት ፊደላቱን ለማጥፋት ከአጥፊዎች ጋር ከሚተባበሩ ጠብቃችኊ ለመጪው ትውልድ የተቀበላችኹትን አደራ እንድታሸጋግሩት ወደ እውነተኛው የጥበብ ብርሃን እንድትደርሱበት ሐሳቤ ነው፡፡
$25.00
ሌላ ዕውነት የለኝም Lela Ewnet Yelegnem By Meron Getnet
ሌላ እውነት የለኝም በተለያየ ጊዜ፣ ቦታ እና ሁኔታ ውስጥ ሆኜ የፃፍኳቸው ግጥሞች ስብስብ ነው። ግላዊ ስሜቶች፣ እውነቶችና በህይወት መስመር ላይ ያስተዋልኋቸው ማህበራዊ ሁነቶች ከጫሩብኝ ሀሳቦች ተነስቼ የከተብኳቸው ናቸው። ጥቂቶቹም በማህበራዊ ሚዲያ ወቅታዊ ጉዳይን ተንተርሰው የቀረቡ ቢሆኑም ጊዜን የሚሻገሩ ሆነው ስላገኘኋቸው በፅሁፍ እንዲነበቡ ስል አካትቻቸዋለሁ። ትወዷቸዋላችሁ።
ሌላ ዕውነት የለኝም Lela Ewnet Yelegnem a book By Meron Ghetnet.
Addis Books




















