Cart

Endihem Tenurual by Abera Lemma 

እንዲህም ተኑሯል Endihem Tenurual a book by Abera Lemma.

የደራሲና ጋዜጠኛ አበራ ለማ ግለ ታሪክ መጽሃፍ በዝነኛው የከተማችን ዘመናዊ የመጽሃፍ መደብር መሸጫ በሆነው በሁሉም የጃዕፈር መጽሃፍት መደብሮች ከቅዳሜ ጥር 23, 2018 ዓ/ም ማግኘት እንችላለን።

February 1, 2026 Amharic 550 pages

Authors

Meet the Author

Abera Lemma

Book By Abera Lemma View All
Endihem Tenurual by Abera Lemma 
abera lemma books

Description

እንዲህም ተኑሯል Endihem Tenurual by Abera Lemma 

ከ1966 ዓ/ም አብዮቱ ከፈነዳበት ማግስት ጀምሮ እስከ ዛሬው የግለ ታሪኩ መጽሃፊ ድረስ ከ21 ያላነሱ የግጥም መድብሎችንና አጫጭር ልቦለዶችን በመፃፍ በአንባቢያን ዘንድ ከፍ ያለ ክብርን ያገኘው አንጋፋው ደራሲ : ገጣሚና ጋዜጠኛ አበራ ለማ የራሱን ግለታሪክ “እንዲህም ተኑሯል” የሚል ርዕስ ጽፎ የተዘጋጀውን መጽሃፍ የካቲት 7, 2018 ዓ.ም በወመዘክር ኅሩይ አዳራሽ የተለያዬ ደራሲያን : ተጋባዥ እንግዶች : የደራሲው ቤተሰብ ወዳጅ ዘመዶቹ በተገኙበት በክብር የሚመረቅ ሲሆን ይህ የደራሲው ግለ ታሪክ መጽሃፍ ለታዳሚው የዳሰሳ ፅሑፍ ከሌሎች ፕሮግራሞች ጋር የሚቀርብ ይሆናል።

ጋዜጠኛ ደራሲ አበራ ለማ በህይወት ዘመኑ በስነጽሁፊ ዘርፍ : በግል ህይዎቱ : በጋዜጠኝነት ሙያው : በኢትዮጵያ በነበሩ የፓለቲካ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ የነበረው ተሞክሮ እውቀት እና ልምድ ለትውልዱ በግለ ታሪኩ ሊያሳውቀን ሊያስተምረን እንዲህም ተኑሯል በሚል ያሳተመውን ግለታሪክ መጽሃፍ በመግዛት ለደራሲና ጋዜጠኛ አበራ ለማ ያለንን ፍቅር አክብሮት እንግለጽለት ።

ይህንን የደራሲና ጋዜጠኛ አበራ ለማ ግለ ታሪክ መጽሃፍ በዝነኛው የከተማችን ዘመናዊ የመጽሃፍ መደብር መሸጫ በሆነው በሁሉም የጃዕፈር መጽሃፍት መደብሮች ከቅዳሜ ጥር 23, 2018 ዓ/ም ማግኘት እንችላለን።

ጋዜጠኛ ደራሲ አበራ ለማ

“…እንዲህም ተኑሯል” የሚል ርዕስ ያለው በ550 ገፆች የተሰናዳው የደራሲና ጋዜጠኛ አበራ ለማ የሕይወት ታሪክ ምረቃ ቅዳሜ የካቲት 14 2018 ዓ.ም በወመዘክር ኅሩይ አዳራሽ ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።
በዕለቱ፣ ታላላቅ እንግዶች በተናጋሪነት የሚጋበዙ ሲሆን በግለ -ታሪክ መፅሀፉም ላይ የዳሰሳ ፅሑፍ ይቀርባል።
አበራ ለማ፣ ካገራችን ገጣሚያንና አጫጭር ልብ-ወለድ ጸሓፊዎች አንዱ ሲሆን በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነፅሑፍ ጥናት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂም፣ ነው።
አበራ፣ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ፕሬስ መምሪያዎች ሠርቷል። ከጦር ግንባር ጋዜጠኝነት እስከ ኪነ-ጥበባት ዘርፎች ሀያሲነት የዘለቀ ሲሆን በአንባቢያን ተወዳጅ የሆኑ ሥራዎችንም ለማስነበብ የቻለ ነው።
ከአበራ ለማ የታተሙ ሥራዎች የሚከተሉት ይጠቀሳሉ።
1967 ኩል ወይስ ጥላሸት፣ የግጥም መድብል፣
1974 ሽበት፣የግጥም መድብል፣
1975 ሕይወትና ሞት፣የአጫጭር ልቦለዶች መድብል፣
1976 ሞገደኛው ነውጤ፣ ኖቭሌት፣
1978 አባደፋር፣ከሌሎች ደራስያን ጋር… ስብስብ፣
1978 ጽጌረዳ ብእር፣ከሌሎች ገጣሚያን ጋር… ስብስብ፣ እና ሌሎችንም ከ21 በላይ መፅሐፍትን ፅፎ ለማስነበብ በቅቷል።
የዚህ መርሐ ግብር የክብር እንግዳ ዶክተር ኃይሉ አርአያ ሲሆኑ ከተናጋሪዎች መካከልም እመቤት ሆይ ፍሬአለም ሺባባው እና ኢንጂነር ቢጃይ ናይከር ይገኙበታል።

Reviews

There are no reviews yet.

Be the first to review “Endihem Tenurual by Abera Lemma ”
AddisBooks Ads