Cart

Authors

Mihret Degif

ምሕረት ደግፍ ትውልድና እድገቷ አዲስ አበባ ፤ በልዩ ስሙ ኮልፌ 18 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በሐምሌ 19 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፣ ሁለተኛ ደረጃን በየካቲት 23 ት/ቤት ፣

Author's Books

Deciding What to Read Next?

Description

ምሕረት ደግፍ ትውልድና እድገቷ አዲስ አበባ ፤ በልዩ ስሙ ኮልፌ 18 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቷን በሐምሌ 19 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ፣ ሁለተኛ ደረጃን በየካቲት 23 ት/ቤት ፣ የመሰናዶ ትምህርቷን ደግሞ በአዲስ ከተማ መሰናዶ ተከታትላ ጨርሳለች። ቀጥሎም በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በመምህርነት በመመረቅ ትምህርቷን ያጠናቀቀች ሲሆን ፤ በአሁኑ ወቅትም በዚሁ ዩኒቨርሲቲ የእንግሊዘኛ ቋንቋ እና ሥነ-ጽሑፍ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪ ናት።

የጋዜጠኝነት ሞያን ከከፍታ የትምህርት ሥልጠና እና የማማከር ተቋም ያጠናቀቀች ሲሆን ፤ በፋክት ቼኪንግ እና ሌሎችም ተያያዥ ሥልጠናዎችን ከሌሎች የሃገር ውስጥ እና የውጪ ተቋማት በሰርተፊኬት ማግኘት ችላለች።

ከመደበኛው ትምህርት ባሻገር ሙሉ የልጅነት ሕይወቷ ያለፈው በደብረ ገሊላ አማኑኤል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ትምህርት ቤት ነው። አሁን ላለችበትም መሰረት የጣለችው ሰንበት ትምህርት ቤት በነበረችበት ወቅት ነው። በተለይም በሥነ-ጽሑፍ ረገድ ዝንባሌ ሊኖራት የቻለው ከልጅነት ጀምሮ በሰንበት ት/ቤት እና በመደበኛ ት/ቤት በነበራት ተሳትፎ ነው። እንደ ግጥም ፣ መነባንብ ፣ ድራማ እና ሌሎችም ላይ የበዛ ተሳትፎ ታደርግ ነበር። ይህ ተሳትፎ አሁንም ድረስ ተከትሏት በመምጣት ለፍሬ እንደደረሰ ታምናለች።

በት/ቤት ፣ በወረዳ እና በክፍለ ከተማ ብሎም በከተማ አቀፍ በነበሩ የሥነ-ጸሑፍ ውድድሮች ፣ መድረኮች እና መሰል ዝግጅቶች ላይ በመሳተፍ የተለያዩ ሽልማቶችን እና የምስጋና ወረቀቶችን ማግኘት ችላለች። በመንፈሳዊም በኩል በተመሳሳይ ሁኔታ በነበሯት ተሳትፎዎች በርካታ ሽልማቶችን አግኝታለች። እስከዛሬ ድረስም በተለያዩ የሥነ-ጸሑፍ መድረኮች ሥራዎቿን እያቀረበች ትገኛለች።

ከኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ እንደተመረቀች በአጼ ፋሲል የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለሁለት ዓመት ያህል በመምህርነት አገልግላለች። በሞያው በቆየችባቸው ጥቂት ዓመታት የተለያዩ የምስጋና እና የደረጃ ሽልማቶችን ማግኘት ችላለች።

ከዚያ በመቀጠል በተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል ለአንድ ዓመት ያህል በፕሮግራም አዘጋጅነት የሠራች ሲሆን ፤ የራሷን መንፈሳዊ ፕሮግራሞች እና ሥራዎች በመሥራት ቆይታለች። በአሁኑ ወቅት በሃገሬ ቴሌቪዥን በከፍተኛ ሪፖርተርነት መደብ እየሠራች የምትገኝ ሲሆን ፤ ላለፈው አንድ ዓመት ያህል በዚሁ ጣቢያ የዜና ክፍል ባልደረባ በመሆን ቆይታለች።

ከልጅነት ጀምሮ የተከተላት የሥነ-ጽሑፍ ፍቅር አሁንም ድረስ ተከትሏት የመጣ ሲሆን ፤ የመጀመሪያ የሆነውንና ” የውቦች ንግሥት” ስትል የሰየመችውን መጽሐፏን ለአንባቢያን ለማድረስ ዝግጅቷን አጠናቃለች።
Mihret Degif was born and raised in Addis Ababa, specifically in the area known as Kolfe 18. She completed her primary education at Hamle 19 Primary School, her secondary education at Yekatit 23 School, and her preparatory education at Addis Ketama Preparatory School. Following that, she graduated with a teaching degree from Kotebe University of Education. Currently, she is pursuing her Bachelor’s degree in English Language and Literature at the same university.
In addition to her academic studies, she completed a journalism training program at Kifta Education Training and Consulting Institute. She has also earned certificates in fact-checking and other related fields from various local and international organizations.

Outside of her formal education, her entire childhood was deeply rooted in Debre Gelila Amanuel Egziabher Meslene Sunday School. It was during her time there that she built the foundation for who she is today. Her passion for literature, in particular, blossomed from an early age through her active participation in both Sunday school and regular school activities. She was heavily involved in poetry, recitations, drama, and other creative expressions, a passion that has stayed with her and finally borne fruit.

Over the years, she has won various awards and certificates of appreciation for participating in literary competitions, stage performances, and events at the school, woreda, sub-city, and city-wide levels. Similarly, she has received numerous awards for her active involvement in spiritual services. To this day, she continues to present her work on various literary platforms.

After graduating from Kotebe University of Education, she served as a teacher at Atse Fasil Primary School for about two years. During her short time in the profession, she received several certificates of appreciation and rank promotions.

Following her teaching career, she worked as a program producer at Tewahedo Media Center for about a year, where she created and hosted her own spiritual programs. Currently, she works as a Senior Reporter at Hagerie Television, having served in the station’s news department for the past year.

The love for literature that has followed her since childhood remains strong, and she has now completed preparations to share her very first book, titled “Yewboch Negest,” with readers.

Review

Customer Reviews

Write A Review

Liyu Ken New Zare - Ethiopian Music

AddisBooks Ads