Author's Books
Deciding What to Read Next?
Description
ደራሲ ጥላሁን ፋንታ፡ በሁለት ትይዩ መስመሮች በጉልህ ይታያሉ በአንደኛው በጤና ባለሙያ በፋርማሲ ዘርፍ በሰው ህይወት በጎ ተፅዕኖ ለመፍጠር፣ በሌላኛው ምዕራፍ ደግሞ በብዕር የህሊናን ድምፅ ለማሰማት—የሚጓዙ የሥነ-ጽሑፍ ሰው ናቸው። ደራሲ ጥላሁን ፋንታ፣ በህይወት ፈተናዎች ውስጥ ያለፉ፣ ውጣ ውረዶችን በንባብ የገሩ፣ እና እውነትን በቃላት የሚስሉ ደራሲ ናቸው።
እ.ኤ.አ. በ1971 ዓ.ም. በቀድሞው ሲዳሞ ክፍለሃገር፣ ጀምጀም አውራጃ (በአሁኑ ጉጂ ዞን፣ ክብረ መንግስት(አዶላ) ከተማ የተወለዱት ደራሲ ጥላሁን፣ እስከ 12ኛ ክፍል ትምህርታቸውን እዛው ተከታትለዋል። የህይወት መንገዳቸው ቀጥተኛ አልነበረም፤ ከማትሪክ በኋላ እንደማንኛውም የክፍለ ሃገር ወጣት ዕጣ ለአስር ዓመታት በንግድና በግብርና ስራዎች ውስጥ የኑሮን መራር ትግል መቅመስ ችለዋል።
በ1998 ዓ.ም. እናታቸውን ተከትለው ወደ ባህር ዳር ያቀኑት ጥላሁን ፋንታ፣ በጋምቢ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በመግባት በፋርማሲ ቴክኒሽያን ሙያ ተመርቀው አዲስ ምዕራፍ ከፈቱ። ትምህርታቸውን አሻስለው ዛሬ ላይ በፋርማሲስትነት በመድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ባህር ዳር ቅርንጫፍ በመጋዘን አያያዝና አስተዳደር ሱፐርቫይዘርነት እያገለገሉ ይገኛሉ።
ገና አምስተኛ ክፍል እያሉ ወደ ስነ-ጽሁፍ ዓለም የገቡት በአደጋ ያጋጠማቸውን የብቸኝነት ስሜት ለመቋቋም መጽሐፍትን እንደ አማራጭ በመውሰድ ነበር። ይህ የንባብ ፍቅር፣ ከጊዜ በኋላ ወደ ጽሁፍ ተቀይሮ የህይወታቸው ዋነኛ መገለጫ ሆነ።
የደራሲ ጥላሁን ፋንታ ስራዎች የትውልድ ታሪክን፣ የግለ-ታሪክ ጥልቀትን እና የህብረተሰብን ነባራዊ ሁኔታ የሚቃኙ ናቸው፡፡ መጀመሪያ እጃቸውን የፈቱት ጓደኞቻቸውን በማስተባበር መዘክረ አዶላ ቅጽ 1 እና ቅጽ 2(መጽሄት – 2014 ዓ.ም.): የትውልድ አከባቢያቸውን የክብረ መንግስትን ከተማ፣ የህዝቧን ህይወት እና የወርቅ ማዕድን ትስስር የሚተርክ በሁለት እትም የታተመ መጽሄት በማዘጋጀት ነው፡፡
ወደ ድርሰቱ ዓለም ከተቀላቀሉ በኋላ ስራዎቻቸውም
• ሰው ብርቱ ብረት ከንቱ (ከዶሎቪያ እስከ ጣና ደንገል) በ2016 ዓ.ም. የህይወት ጉዟቸውን የሚያሳይ፣ ባለ 220 ገጽ ያለው ግለ-ታሪክ።
• የቡና ቤት ንቦች (በ2017 ዓ.ም.): በህብረተሰቡ ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ የተቃኙ ወጎች የተካተቱበት፣ባለ 219 ገጽ መጽሐፍ።
• ጥቁር ገጽ (በቅርብ ቀን): የህሊናን ድምፅ የሚመረምር፣ ለታዳሚው በጉጉት የሚጠበቅ 309 ገጽ ያለው አዲስ ኢ-ልብወለድ ስራዎች አሏቸው።
የጥላሁን ፋንታ ስራዎች ተራ ታሪኮች አይደሉም፤ የህሊናን ድምፅ የሚመረምሩ፣ ለሰብአዊ ክብር የሚቆሙ ጥበቦች ናቸው የ”ውስጠ ወይራ” (Allegory) ጥበብ: ቀጥተኛ ንግግር በማይበጅበት ጊዜ፣ እውነትን በምሳሌና በተምሳሌት ጠቅልሎ አንባቢው በራሱ አስተውሎት እንዲፈታው ይጋብዛሉ። የሰብአዊ ክብር (Human Dignity) ሞጋች: ገጸ-ባህሪያቶቻቸው ተጎጂ ሆነው አይቀሩም። በሁኔታዎች ተገደው እንኳን የራሳቸውን ክብር የሚጠብቁ፣ የውስጥ ጥንካሬ ያላቸው አሸናፊዎች ናቸው። የህሊና ጩኸት: ሰው ትልቁ ጠላቱ የሆነውን “ዝምታ” በብዕራቸው ይሰብራሉ። የውስጣዊ ግጭትን እና የህሊናን ወቀሳ በጥልቀት ይዳስሳሉ። ስሜት ቀስቃሽ አጻጻፍ: ቋንቋቸው ቀላል ቢሆንም፣ አንባቢው በገጸ-ባህሪው ስሜት ውስጥ ዘልቆ እንዲገባ የሚያደርግ ደፋር የቃላት ምርጫ አላቸው።
ደራሲ ጥላሁን ፋንታ በዝምታ የተከበበን እውነት በቃላት ጩኸት የሚገነጥል ብዕር የተጎናጸፉ ጸሐፊ ናቸው፡፡
Review
Customer Reviews
For This Month
The Best Authors
Abere Shiferaw
Kalkidan Hailu Gebre
Simegn Gizaw Bedada
Tersida Wondemu
Dr. Ashenafie Tsegaye
Azaries Dessie
AddisBooks Ads


Write A Review