Author's Books
Deciding What to Read Next?
Description
ዶ/ር ፈቃዱ ፉላስ አዲስ አበባ ተወልዶ አዲስ ከተማ ውስጥ አደገ:: ቅድመ-ኮሌጅና የኮሌጅ ትምህርቱን የተከታተለው እዚያው አዲስ አበባ ውስጥ ነው:: የመጀመሪያ የፋርማሲ ዲግሪውን ካገኝና ከጥቂት ዓመታት ሥራ በኋላ ወደ ቺካጎ ተጉዞ የዶክትሬት ትምህርቱን በዪኒቨርስቲ ኦፍ ኢሊኖይ አጠናቀቀ:: የትምህርት ዘርፉ ፋርማሲ ሆኖ፣ ነገር ግን በተፈጥሮ መድኃኒቶች ላይ ያተኮረ ነበር:: ቀጥሎም ሰሜን ካሮላይና በሚገኘው ሪሰርች ትሪያንግል ኢንስቲትዪት የድኅረ ዶክትሬት ስልጠና ተከታተለ:: በዚያው ተቋም ውስጥ በሪሰርች ኬሚስት ደረጃ በርካታ ምርምሮችን አካሄደ:: ከዚያ ተከትሎ ትኩረቱን ወደ ክሊኒካል ፋርማሲ በማዞር ለብዙ ዓመታት የፋርማሲ ምሩቃንን ክሊኒካል ምርምር በማስተባበር ሰራ::
ዶ/ር ፈቃዱ በአካዳሚክ የህይወት ዘመኑ በርካታ ጽሑፎችን አካፍሏል:: ቁጥራቸው ከ 180 በላይ የሚሆኑት ጽሑፎቹ መጻሕፍትን፣ የመጻሕፍት ምዕራፎችን፣ የምርምር ወረቀቶችን፣ የተለያዪ ዘገባዎችን እንዲሁም ሌሎች አበርክቶዎችን ያጠቃልላሉ:: ዶ/ር ፈቃዱ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ አሶሲዬት ፌሎው ነው ያበረከታቸው መጻሕፍት በአሮፓያውያን አቆጣጠር በ 2001 ይጀምርና አስከዛሬም ቀጥሏል::
Review
Customer Reviews
For This Month
The Best Authors
Serk Daniel / Daniel Gobena
1 Book
Natnael Kerealem
3 Books
Hamrawit Tesfa
2 Books
Meseret Bahru
1 Book
Solomon Abebe
1 Book
Prime Minister Abiy Ahmed
1 Book
AddisBooks Ads


Write A Review