Cart

  • Home
  • Business

Denbegnalogy: From Experience to Excellence By Yonas Nigussie Abebe

 ደንበኛሎጂ  ከልምድ ወደ ልቀት  በዮናስ ንጉሤ አበበ.

Addis Books!

September 10, 2026 Amharic

Description

አዲስ መጽሐፍ  ደንበኛሎጂ  ከልምድ ወደ ልቀት  በዮናስ ንጉሤ አበበ
በአሁኑ የገበያ ውድድር ውስጥ ተመሳሳይ ምርቶችን በየቦታው ማግኘት ቀላል ሆኗል። ነገር ግን አንዱን ድርጅት ከሌላው ለይቶ የክብር ማማ ላይ የሚሰቅለው የትኛው እንደሆነ ያውቃሉ? የአገልግሎት ጥራት እና የደንበኛ አያያዝ!
ፈገግታ፣ መልካም ስነ-ምግባር፣ ተገቢ አለባበስ እና ለማገልገል የሚኖረን ቀናነት ዝም ብለው የሚወጡ የንግድ ወጪዎች አይደሉም፤ ይልቁኑ የድርጅታችንን ስም በገበያው ላይ በጠንካራ መሠረት ላይ የሚገነቡ ትርፋማ ኢንቨስትመንቶች ናቸው። ደንበኛ ከአንድ ድርጅት የሚርቀው ስለ ምርቱ ጥራት ሳይሆን በተደረገለት መስተንግዶ ስለሚሰማው ስሜት ነው። አቀባበላችን፣ አለባበሳችን እና አነጋገራችን በደንበኛው ልብ ውስጥ የማይረሳ አዎንታዊ ምስል የመቅረጽና የመለወጥ ትልቅ ኃይል አላቸው።
ዛሬ ያለንበት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘመን ደግሞ የነገሮችን ፍጥነት ቀይሮታል። እያንዳንዱ መስተንግዶ በዓለም ዙሪያ የመሰራጨት ዕድል አለው። አንድ ጥሩ አገልግሎት በአጭር ጊዜ ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ወደ እኛ ሊስብ እንደሚችል ሁሉ፣ አንድ መጥፎ አቀባበልም እንዲሁ የድርጅቱን ስም በአንዴ ሊያጠፋ ይችላል። ስለዚህ የአገልግሎት ባህላችንን ወደ ስልታዊ ደረጃ ማሳደግና በየቀኑ ለላቀ ስነ-ምግባር መተጋት የህልውናችን ጉዳይ ነው።
ይህ መጽሐፍ እነዚህን ወሳኝ የዘመናችንን የአገልግሎት ጥበቦች እና የቴክኖሎጂ ሽግግሮች ከተግባራዊ ልምምድ ጋር አዋህዶ ይዞላችሁ ቀርቧል!
መጽሐፉ ለማን ተዘጋጀ?
  • ለድርጅት መሪዎች እና ሥራ አስኪያጆች
  • ለሥራ ፈጣሪዎች እና ነጋዴዎች
  • በሽያጭ፣ በማርኬቲንግ እና በመስተንግዶ ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሙያዎች

 መጽሐፉን በየመጽሐፍ መደብሩ ያገኙታል!

Reviews

There are no reviews yet.

Be the first to review “Denbegnalogy: From Experience to Excellence By Yonas Nigussie Abebe”