The Adventure of Piny by Liron Michael
The Adventure of Piny by Liron Michael. Addis Books!
Yewboch Negest የውቦች ንግሥት by Mihret Degif
Yewboch Negest የውቦች ንግሥት by Mihret Degif. Addis Books!
Eneman Neberu እነማን ነበሩ? by Alemayehu Mammo
Eneman Neberu እነማን ነበሩ? by Alemayehu Mammo. Addis Books!
Karamon Pigeon and Falcon ካራሞን ዋኖስ እና ጭልፊት by Azaries Dessie
Karamon Pigeon and Falcon ካራሞን ዋኖስ እና ጭልፊት by Azaries Dessie . Addis Books!
ወሪሳ (የውድቀት ፈለጎች) Werisa (Yewidket Felegoch)
Werisa (Yewidket Felegoch) (Paper Cover) ወሪሳ (የውድቀት ፈለጎች) By Alemayehu Gelagay
አንድ የአማርኛ መምህር ከአርሲ ነገሌ በሰራ ቅያሪ አዲስ አበባ ወደምትገኝ ወሪሳ በምትባል ሰፈር አክስቱ ለጊዜው ወዳወረሱት ቤት ይገባል:: መምህሩ በዚህች ሰፈር እንዲሁም በጎረቤት ሰፈሯ "እሪ በከንቱ" የሚያጋጥመውን የመላመድና የመኖር ፈተና ፣ ግጭት ፣ መስማማት ፣ ተንኮል ፣ ፍቅር ፣ አጣብቂኝ ፣ ውዝግብ ፣ እንዲሁም የሚሰማቸውን ወግና ታሪክ(ተረት) ይተርካል::
መፅሐፉ የሚያነሳችው ወጎች ፣ ተረትና ምሳሌዎች ፣ ታሪኮች(ተረቶች) ተምሳሌያዊነትን ያዘሉ ሲሆን የኢትዮጵያን ያለፈ እና የአሁኑን ታሪክ: የአሁኑ ትውልድ የሚያይበትን የተዛባ ዓይን ፣ በአሁኑ ትውልድ ውስጥ ስላሉት የተለያዩ ነባራዊ ሐቆች እንዲሁም ልዩነት ያላቸው ተጎራባቾች ላለፈው ታሪክ የሚያድርጉትን ሽሚያ እና ሽኩቻን ያሳያል::
$5.99
አልተዘዋወረችም Altezewawerechim
ፍቅር ሁሉ ፍቅር አይደለም። በደፈናው አፈቀርን ወይም ተፈቀርን እንበል እንጅ ሰዎች ምናችንን በምን ምክንያት እንደወደዱልን በእርግጠኝነት መናገር የሚቻል ነገር አይደለም። ሰዎች ከማንነት በላይ ለአካላዊ ውበት በፍቅር ሊወድቁ ይችላሉ፤ ምናልባትም ይህ ለራሳቸውም አይገባቸውም ይሆናል። ከነጭራሹ «ወደድናችሁ» ያሉን ሰዎች እንደወደዱን ማረጋገጫችንስ ምንድነው ? ትዳር ? ስጦታ? ቃልኪዳን? ለእኛ የሚከፍሉት መስዋዕትነት? በመኖር ብቻ የሚመለስ ጥያቄ ሳይሆን አይቀርም። በዚህ መፅሐፍ ከነመኖራቸው ትዝ የማይሉን ጥቃቅን ስሜቶች ስንጥቃቸው እየሰፋ ሕይዎትን ለከባድ ምስቅልቅል ሲዳርጉ እናያለን። «ምናለበት» ተብለው ችላ የተባሉ እንደውም እንደበጎ ነገር የሚታዩ ጉዳዮች በጥልቀት ሲቃኙ ያላቸውን አደገኛ ስር እንመለከታለን። በሕይዎት ውስጥ « ቁጭ ብለን የሰቀልነውን ቁመን ማውረድ ሲያቅተን» ሌሎች ድሎት ያሉት ነገር ለሌላው መከራ ሲሆኑ ፣ እንታዘባለን። ፅናት፣ ፍቅር ፣ ስደት ፣ናፍቆት ፣ዓላማ ፣ ሐዘን ፣ደስታ ፣ በውብ ትረካ ተሰድረው እናገኛቸዋለን። እንደቀላል የልጅነት ሁዳዳችን ላይ የተጣለች ቅንጣት የቃል ዘር በኋለኛው ዘመናችን ዛፍ ሁና ጥላዋን በአኗኗራችን ላይ ስታጠላ እንታዘባለን። በመጨረሻም መፅሐፉን ስንከድን የራሳችንን ሕይወት ከፍተን መመልከት እንጀምራለን።
$5.99
ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ሕይወትና ክህሎት
ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ሕይወትና ክህሎት በዓለማየሁ ገላጋይ
The life of Sebhat Gebre-Egziabher and his skills book by Alemayehu Gelagay
የዓለማየሁ ገላጋይ ሥራዎች:
"ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ሕይወትና ክህሎት"፣ "ቅበላ"፣ "የብርሃን ፈለጎች"፣ "ኢህአዴግን እከሳለሁ"፣ "ኩርቢት"፣ "ወሪሳ"፣ "አጥቢያ"፣ "የፍልስፍና አፅናፍ"፣ "በፍቅር ስም"፣ "መለያየት ሞት ነው"፣ "በእውነት ስም (ታለ)"፣ "ውልብታ"፣ "በእምነት ሥም(ሐሰተኛው)"፣ "የተጠላው እንዳልተጠላ" "ቤባኒያ (ዕውነት ሐሰት)"፣ "ማዕበል ጠሪ ወፍ"፣ የተሰኙ ልቦለድና ኢልቦለድ መፃሕፍት ለአንባቢያን አበርክቷል። ከዚህ በተጨማሪም "መልክዓ–ስብሐት" በተሰኘው መጽሐፍ 27 ጸሐፊያን፣ ደራሲያን፣ ገጣሚያንና ሰዓሊያን አሳትፎ በማሰናዳት ለአንባብያን አድርሷል።
$5.99














