Cart

Shop

Miteralion book by Alemayehu Wassie
Miteralion book by Alemayehu Wassie

ሚተራሊዮን: Miteralion

ሚተራሊዮን: Miteralion book by Dr.Alemayehu Wassie Eshete ከመጽሃፉ የተወሰደ ...." አንድ ሁለት መቶ ሜትር እንደተጓዙ አንድ ጫማ በላይ በአንድ ጊዜ የማታስረግጥ የበሬ ምላስ የምታክል የሠርጥ መንገድ ተከትለው መውረድ ጀመሩ፡፡ በግራ በኩል ጭው ያለ ገደል በቀኝ በኩል ደግሞ የሚያዝ የሚጨበጥ የሌለው ዐለት ከመንገዱ ጥበትና ተዳፋትነቱ ተጨማምሮ “‹ወደ ጽድቅ የሚወስደው መንገድ ጠባብ ነው› የተባለው ይሄ ይሆን?” አልኩ፡፡ ትንሽ እንደተራመድን ለመውረድ ሰውነቴ ሲንቀጠቀጥ " …. ….. "አባ መዐዛ መንገድ ላይ ስንመጣ ስለ ኢነርጂ ዲስፔሽን የጠየቀኝ ትዝ አለኛና ‹ይሄ ሰው ስለዚህ ስፍራ ቀደም ብሎ መረጃ ነበረው ማለት ነው? እነዚያ ቦታዎችም ማስተንፈሻ ናቸው ማለት ነው?› አልኩ ለራሴ ….."
$29.99
Sebez-Dr.-Alemayehu-Wassie
Sebez-Dr.-Alemayehu-Wassie

ሰበዝ: Sebez

ሰበዝ: Sebez 

$27.65
ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ሕይወትና ክህሎት Alemayehu Gelagay
Alemayehu Gelagay
Hot

ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ሕይወትና ክህሎት

ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ሕይወትና ክህሎት በዓለማየሁ ገላጋይ The life of Sebhat Gebre-Egziabher and his skills book by Alemayehu Gelagay   የዓለማየሁ ገላጋይ ሥራዎች: "ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ሕይወትና ክህሎት"፣ "ቅበላ"፣ "የብርሃን ፈለጎች"፣ "ኢህአዴግን እከሳለሁ"፣ "ኩርቢት"፣ "ወሪሳ"፣ "አጥቢያ"፣ "የፍልስፍና አፅናፍ"፣ "በፍቅር ስም"፣ "መለያየት ሞት ነው"፣ "በእውነት ስም (ታለ)"፣ "ውልብታ"፣ "በእምነት ሥም(ሐሰተኛው)"፣ "የተጠላው እንዳልተጠላ" "ቤባኒያ (ዕውነት ሐሰት)"፣ "ማዕበል ጠሪ ወፍ"፣ የተሰኙ ልቦለድና ኢልቦለድ መፃሕፍት ለአንባቢያን አበርክቷል። ከዚህ በተጨማሪም "መልክዓ–ስብሐት" በተሰኘው መጽሐፍ 27 ጸሐፊያን፣ ደራሲያን፣ ገጣሚያንና ሰዓሊያን አሳትፎ በማሰናዳት ለአንባብያን አድርሷል።
$5.99
ሶምሶማ Somsoma by Sirak Wondemu 
ሶምሶማ Somsoma by Sirak Wondemu 

ሶምሶማ Somsoma by Sirak Wondemu 

ሶምሶማ Somsoma, a book by Sirak Wondemu . በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ሶምሶማ የተሰኘው አዲስ መፅሐፍ አሁን ለንባብ በቅቷል። ይህ መፅሐፍ እንደ ስሙ ሁሉ በህይወት፣ በታሪክ እና በማህበራዊ ክስተቶች ውስጥ እያስጎበኘ በዝግታና በጥልቀት የሚያሰላስሉ ድንቅ ስራዎችን አዝሏል። Addis Books
$400.00
be Misrak bekul solomon sahele
Solomon sahele
Hot

በምሥራቅ በኩል By Solomon Sahele Tizazu

በምሥራቅ በኩል Be Misrak Bekul a book By Solomon Sahele Tizazu. ዋጋ: 500 ብር በሚከተሉት የባንክ አካውንቶች ይጠቀሙ: በአድራሻዎ ይደርስዎታል:: 1000025047447 CBE ሰለሞን ሳኅለ (ሶል) በግጥሞቹ ነፍሳችንን ሲያባባ፣ በአጫጭር ልቦለዶቹና በወጎቹ ደግሞ ስሜታችንን ሲገዛ ቆይቷል። አሁን ግን ረዥም፣ ዝርው እና እውነተኛ ታሪክን መሠረት ባደረገው “በምሥራቅ በኩል” በተሰኘ አዲስ ሥራው ብቅ ብሏል። ሶል ወደ አዲሱ የጽሕፈት ዘውግ ሲሻገር ማየት ለሁላችንም ትልቅ ጉጉት ነው።
$10.00
ተድባብ Tedbab by Hiwot Teffera
Tedbab by Hiwot Teffera books

ተድባብ Tedbab by Hiwot Teffera

ተድባብ Tedbab, a book by Hiwot Teffera.
ከመጽሐፉ የተወሰደ ‹‹ሰው እንዲህ ነው ማለት ይቻላል የኔ ልዥ? ዕድሜህ እየገፋ ሲኸድ ዝጌር ተፈጠራቸው መሀል ሁሉ ሚስጥሩ ሰው እንደሆነ ትረዳለህ። የምንደራችን ሰዎች እርስ በርስ እየተላለቁ ምንደራችንን የወላድ መካን አርገዋል። ወንድም ወንድሙን ጭምር እየገደለ ሞትን ንቀዋል። ኻወቁ ግና ሞት አይናቅም። ጦር ሜዳ ላይ ሞት የሰውን ልዥ ሲንቅ አይቻለሁ።›› የደራሲዋ ቀደምት ስራዎች:-
  1. Tower in the Sky
  2. Mine to Win
  3. ምንትዋብ
Addis Books!
$25.00