Description
by Dr Shimelis Wondimu
እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ። በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፥ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤ የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤ እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤ ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን” (ማቴ.6:9-13)። አንድ ሰው ስለ ጸሎት ሊያውቃቸው የሚገባ መሰረታዊ ሃሳቦች አሉ፡፡ ወደ ማን ነው መጸለይ የሚገባው? ማን ነው መጸለይ የሚችለው? እግዚአብሔር የሚመልሰውና የማይመልሰው ጸሎት ምን አይነት ነው? እንዴት መጸለይ አለበት? መቼ? በምን አይነት ሁኔታ? እንዴት እንጸልይ? የሚለውን ጥያቄ መመለስ ውጤታማ ያደርጋል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ጸሎትን አስተምረን ባሉት ገዜ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በጥያቄያቸው መሠረት አስተማራቸው፡፡ ከዚህ የምናየው ጸሎት የምንማረው እና በእውቀት ልናደርገው የሚገባ እንደሆነ ነው፡፡ የጸሎትን መርሕ ማወቅ ለስኬታችን ይረዳናልና። የገባኝን ላካፍላችሁ ይህንን ጽፌአለሁ። መልካም ንባብና መልካም ጸሎት!
ሽመልስ ወንድሙ
Reviews (0)
You must be logged in to post a review.
AddisBooks Ads









Reviews
There are no reviews yet.